07/11/2022
...ከራስህ ተሞክሮ በመነሣትም ታውቀዋለህ። በስቃይ፣ በእንግልት ውስጥ ስትሆን እግዚአብሔርን ታስታውሳለህ። ደስተኛ ስትሆን፣ ሕይወትም ፈንጠዝያ ስትሆን ስለፈጣሪ ምንም አትጨነቅም፤ አታስታውስምም። ቀላል ተሞክሮ ነው፤ ለማየት ሳይኮሎጂስት አያስፈልግም። ሁሉም በራሱ ሕይወት ሊያስተውለው ይችላል።
በርግጥ ነገሮች ጥሩ ስሄዱ ወደ ቄስ ሄደህ አታውቅም ነበር። ነገሮች ውብ ሆነው ስሄዱ፣በሕይወትም ስኬታማ ስትሆን፣ ሕይወትም የአበባ ማስቀመጫ ስትሆን፣ ፈጣሪን አላስታወስክም። ሕይወት የብስጭት ቦታ ስትሆን ግን በድንገት እግዚአብሔርን ታስታውሳለህ።
#እግዚአብሔር ማምለጫህ ይሆናል።
👇
Telegram: Contact @EthioOsho
04/11/2022
አንተ ትክክል መሆን አለመሆንህን ለማወቅ የህሊናህና የድርጊትህ እንጂ የሌሎች ሰዎች ድጋፍና ምስክርነት አያሻህም ትክክለኛዉን እንጂ አብዛኛውን ለመሆን አልተፈጠርክምና!"
መቶበመቶ ትክክለኛ ባትሆን እንኳን መቶበመቶ የሌላ ቅጂ አትሁን!
#ኦሾ
Osho
You can view and join right away.
03/11/2022
“የፈጣሪ ያለህ … ጭራሽ #ፍልስፍና የምትማረው የፈላስፎችን መንገድ ለመዋጋት ነው? እንዲህ አይነት ነገር ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም፡፡ ፍልስፍና እማራለሁ የምትል ከሆነ ብር የሚልክልህን ፈልግ” አሉኝ፤
እኔም ተዉት አልኳቸው !!!
…
ከማትሪክ ውጤት በኋላ መላው ቤተሰቤ ተበጠበጠ … ምክንያቱም አንዱ ዶክተር እንድሆን ይፈልጋል፣ አንዱ ሳይንቲስት እንድሆን ይፈልጋል፣ ሌላው መሐንዲስ እንድሆን ይሻል፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ሙያዎች ሕንድ ውስጥ በጣም የሚያስከብሩ፣ ‘የሚያበሉ’ የሚባሉ ሙያዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሙያዎች ውስጥ ከገባህ #ሃብታም፣ ዝነኛ፣ የተከበርክ ትሆናለህ ነው የሚሉት፡፡
እኔ ግን “የማጠናው ፍልስፍና ነው…” ስላቸው ሁሉም ጮሁ፡፡
“አብደሃል ? የማይሆን ነገር ነው የምታወራው !! ማንም ሰው ሞኝ ካልሆነ በስተቀር ፍልስፍና ላጥና አይልም፡፡ ፍልስፍና ተምረህ ምን ለመሆን ነው ? ስድስት ዓመት ሙሉ ዋጋ የሌለው ነገር እየተማርክ ጊዜህን በከንቱ ልታጠፋ ነው ማለት ነው፡፡ ፍልስፍና እማራለሁ ብለህ ከንቱ ሆነህ እንዳትቀር፡፡ ተራ ሥራ እንኳ አታገኝም…”
እናም ትክክል ናቸው፡፡
ሕንድ ውስጥ ተራ ለሚባል ሥራ፣ የ12ኛ ክፍል የማትሪክ ወረቀት ብቻ ለሚጠይቅ የፖስታ አመላላሽነት ሥራ፣ በፍልስፍና የማስተርስ ዲግሪህን፣ ከዩኒቨርሲቲው አንደኛ የወጣህበትን የወርቅ ሜዳሊያህን ብታቀርብ፣ ማንም እሺ ብሎ የሚቀጥርህ የለም፡፡ አዎ … በነዚህ ባቀርብካቸው ነገሮች ሳቢያ እምቢ ትባላለህ !!! ያቀረብካቸው ነገሮች የብቃት ማረጋገጫ ሳይሆኑ #አደገኛ ሰው ነህ ማለት ነው !!! ‘ሆ … ለፖስታ አመላላሽነት ፈላስፋ ቀጥረን ደግሞ እንቃጠል እንዴ…’ ነው የሚሉት !!!
“እድሜ ልክህን ችግር ውስጥ ነው የምትገባው - ብታስብበት ይሻላል” አሉኝ…
“ፈፅሞ #አላስብበትም፡፡ ደግሞ ታውቁኛላችሁ፡፡ እኔ በቀጥታ ነው የማየው፡፡ ምርጫ የሚሉት ነገር እዚህ ውስጥ አይገባም፡፡ ምን ማጥናት እንዳለብኝ እኔው ራሴ ነኝ የማውቀው፡፡
የትኛው ሙያ ያዋጣል አያዋጣም የእኔ ጉዳይ አይደለም፡፡ ለማኝ ብሆን እንኳ ፍልስፍና ማጥናቴን አልተውም” ስላቸው፣
ምን እንደሚሉ ግራ ገባቸው፡፡
“ቆይ ግን” አሉኝ፣ “ለመሆኑ ለምንድነው ፍልስፍና ለመማር የፈለግከው ?”
“ምክንያቱም መላው ሕይወቴን ከፈላስፎች ጋር ፍልሚያ እገጥማለሁ፡፡ ስለዚህም ስለእነሱ ሁሉንም ነገር ማወቅ እፈልጋለሁ”
“የፈጣሪ ያለህ…” አሉ፣ “ይሄ ነው ምክንያትህ ? በቃ ? አንድ ሰው የፈላስፎችን ሐሳብ ለመዋጋት በሚል ፍልስፍና እንደሚያጠና አናውቅም ነበር !!! ይሄ ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ ነገር ነው”
“እስከዛሬ ካልሰማችሁት እንግዲህ አሁን ከእኔ ስሙታ … ከፈላስፎች ጋር ፍልሚያ እገጥማለሁ - እድሜ ልኬን፡፡ ለዚህ ደግሞ ፍልስፍና ማጥናት አለብኝ፡፡ የፍልስፍና #የክርክር ስልቶች በጣም ነው የሚጥሙኝ፡፡ ስለዚህም የእያንዳንዱን ፍልስፍና የክርክር ነጥቦች በጥልቀት መመርመር እፈልጋለሁ፡፡
ጠልቄ ማየት እሻለሁ፡፡ ዋንኛ ዓላማዬ ግን ፈላስፎችን መፋለም ነው፡፡ ምክንያቱም ከልምዴ እንዳየሁት አንድም የበራለት (Enlightened) ፈላስፋ የለም፡፡ እንዲሁ ነው በቃላት የሚጫወቱት፤ በአመክንዮ ጅምናስቲክ የሚተጣጠፉት፡፡ መቼም ከአንጎላቸው በላይ ወጥተው አያውቁም፡፡ በአንጎላቸው ትልልቅ ሥራዎች ሰርተዋል - ግን አእምሮ ብቻ ሆነው ቀርተዋል”
ነገር ግን … ያው … እብድ ብጤ መሆኔን ስለሚያውቁ፣ “ለነገሩ እንደዚህ አይነት ነገር እንደምታደርግ የሚጠበቅ ነው” አሉ፡፡
ቢሆንም የቻሉትን ያህል ሞከሩ፡፡
“ጊዜ አለ … እስቲ አስብበት … ዩኒቨርሲቲዎቹ እስኪከፈቱ አንድ ወር ያህል ጊዜ ስላለ አስብበት” አሉኝ፡፡
“አንድ ወርም፣ አንድ ዓመትም፣ አንድ ሕይወትም ለውጥ የለውም - ምክንያቱም እኔ አልመርጥም፡፡ ይህ የእኔ ምርጫ አልባው ኃላፊነቴ (choiceless responsibility) ነው”
ከአጎቶቼ አንዱ እንዲህ አለ [የዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ነው]፣ “ከእሱ ጋር መነጋገር በጣም ከባድ ነው፡፡ ምንም ትርጉም ያላቸው የማይመስሉ ቃላት ነው የሚጠቀመው፡፡ ምርጫ አልባነት … ኃላፊነት … ንቃተ ሕሊና - እነዚህን ነገሮች ከሕይወት ጋር ምን ያገናኛቸዋል ? እንዴ … ገንዘብ ያስፈልግሃል፣ ቤት ያስፈልግሃል - #ቤተሰብ መስርተህ ቤተሰብህን መደገፍ አለብህ”
“ቤተሰብ አልመሰርትም፤ ቤትም አይኖረኝም፣ ማንንም አልደግፍም” አልኩት፡፡
እናም ማንንም አልደግፍም፤ ቤትም አልሰራሁም፡፡ የዓለማችን የመጨረሻው ደሃ ሰው ማለት እኔ ነኝ፡፡
ዶክተር፣ ኢንጂነር ወይም ሳይንቲስት ሊያደርጉኝ ሞክረው ስላልተሳካላቸው በጣም ተናደዱ፡፡
እናም ሊያስፈራሩኝ ሞከሩ፤ “ፍልስፍና የምታጠና ከሆነ ገንዘብ አንልክልህም” አሉኝ፡፡
“እንዲህ ማለትም አይጠበቅባችሁም፡፡ እኔም ራሴ አልቀበላችሁም፡፡ #ምክንያቱም የምማረው ራሴ የመረጥኩትን አይደለ ? ስለዚህ ራሴው እወጣዋለሁ፡፡ እናንተ ተማር ያላችሁኝን አልመረጥኩም፡፡ ስለዚህ ከእናንተ ገንዘብ መቀበል የማይታሰብ ነው፡፡ ለምን ብዬ ነው ገንዘብ ከእናንተ የምቀበለው ? ለምን ብዬ ? ብትሰጡኝም አልቀበልም” ስላቸው፣
ክው አሉ…
እንዴት ብሎ ይችለዋል ብለው ነበር - እኔ ግን ቻልኩት፡፡ ለሊት ጋዜጣ ላይ አዘጋጅ ሆኜ እሰራለሁ፡፡ ቀን ዩኒቨርሲቲ እማራለሁ፡፡ በዚህ መሃል ባገኘሁት አጋጣሚ እተኛለሁ፡፡
በስተመጨረሻ #ጥፋተኝነት ተሰማቸው፡፡ አባቴ፣ “እባክህን ይቅርታ አድርግልንና የላክንልህን ገንዘብ ተቀበል” እያለ ይፅፍልኛል፡፡
በፖስታ ቤት የሚልኩልኝን የገንዘብ ማዘዣ መልሼ እልክላቸዋል፡፡ አንድ ቀን አባቴ ዩኒቨርሲቲ ድረስ መጥቶ፣ “ይቅርታ አታደርግልንም ? እባክህን ሁሉን ነገር እርሳው” አለኝ፡፡
“ይቅር ልል እችላለሁ፡፡ ግን መቼም አልረሳውም” አልኩት፣ “ምክንያቱም በገንዘብ አስገድዳችሁ የማልፈልገውን ትምህርት እንድማር ልታደርጉኝ ሞክራችኋል…” ለእነሱ ገንዘብ ትልቅ ነገር ነው፡፡
“ከእኔ ይልቅ ገንዘባችሁ ነው ያሳሰባችሁ፡፡ እናም አስፈራራችሁኝ፡፡ ከእናንተ ገንዘብ አልፈልግም፡፡ እዛው ያዙት ብራችሁን፡፡ እኔ በደምብ እየኖርኩ ነው”
አባቴ ገንዘቡን የማትቀበለኝ ከሆነ ከዚህ አልሄድም አለ፡፡
በእኔ ምክንያት ማንም ሰው ጥፋተኛነት እንዲሰማው ስለማልፈልግ ገንዘቡን ተቀበልኩት፡፡
Source: Osho
#ኦሾ and please
Telegram: Contact @EthioOsho
02/11/2022
“እነሆ ሁላችሁም ባላችሁበት ከዩኒቨርሲቲው በከፍተኛ ማዕረግ አንደኛ ወጥተሃል ብላችሁ የሰጣችሁኝን የወርቅ ሜዳሊያ የውሃ ጉድጓድ ውስጥ እጨምረዋለሁ፡፡ ማንም ሰው እንዲቀናብኝ አልፈልግም፡፡ ይኸው፡ የወርቅ ሜዳልያውን የውሃ ጉድጓድ ውስጥ ጨመርኩት፡፡
ከዚህ በኋላ እኔ ማንም ነኝ፤ ማንም ሊቀናብኝ አይችልም፡፡ ቅናት የሚፈለፈለው ከማወዳደር ነው፡፡ ማንም ከማንም አይበላለጥም፡፡ ሁሉም ሰው በራሱ ሙሉዕ ነው፡፡ አንዱ በሆነ መስክ ከሌሎች ሊሻል ይችላል፤ ሌላው ደግሞ በሌላ መስክ ልቆ ይገኛል፡፡
ይሄ ደግሞ ሰዎች የተለያየን መሆናችንን ነው የሚያሳየው፤ ውድድር እዚህ ውስጥ ፈጽሞ አይገባም፡፡ ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ ማንም ነኝ፡፡ ማንም ሊቀናብኝ አይችልም፡፡ የወርቅ ሜዳሊያውን የውሃ ጉድጓድ ውስጥ ጨምሬዋለሁ - አበቃ”
#ኦሾ፣ ከዛሬ 50 ዓመት በፊት በአንዲት ማለዳ ከሚማርበት ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ማዕረግ አንደኛ በመውጣት የተሰጠውን የወርቅ ሜዳሊያ መላው የዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰሮችና ተመራቂ ተማሪዎች በተገኙበት የዩኒቨርሲቲው የውሃ ጉድጓድ ውስጥ ሲጨምር የተናገረው…
and 🙏
Osho
You can view and join right away.
01/11/2022
#ቅናት ውድድር ወይም ንጽጽር ነው፡፡ እንድናወዳደር እና እንድናነጻጽር ተምረናል፡፡ ሁሌም እንድናነጻጽር ተገርተናል፡፡
👉 አንድ ሰው የተሻለ ቤት አለው፡፡
👉 አንድ የሆነ ሰው ያማረ አካል አለው፡፡
👉 አንድ ሌላ ሰው ብዙ ገንዘብ አለው፡፡
👉 አንድ ሰው ማራኪ ስብእና አለው።
ራሳችሁን ከአላፊ አግዳሚው ጋር አነጻጽሩ እናም ታላቅ ቅናት የሚያንሰራራ ይሆናል፡፡
ቅናት የንጽጽር ውጤት ነው፡፡ ንጽጽርን እና ውድድርን የምታስወግዱ ከሆነ ቅናት ይጠፋል። ከዚያም ራሳችሁን እንደሆናችሁት ብቻ ታውቁታላችሁ፡፡
እናንተ ማንንም አይደላችሁም፡፡ ማንንም መሆን አያስፈልጋችሁም። #ውድድር እና #ንጽጽር በጣም ቂላቂል አመላካከት ነው ምክንያቱም እያንዳንዱ ሰው ልዩ እና የማይነጻጸር በመሆኑ ነው፡፡
ይህ ግንዛቤ አንድ ጊዜ በውስጣችሁ ከሰፈነ ቅናት ይጠፋል፡፡
እያንዳንዱ ሰው ልዩ እና የማይወዳደር ነው። እናንተ ራሳችሁን ብቻ ናችሁ። ማንም ፈጽሞ እናንተን አይመስልም፡፡
እናንተም ፈጽሞ ማንንም መምሰል አትችሉም።
#ኦሾ
Please and
https://t.me/EthioOsho