31/10/2022
ተመስገን ተመስገን ተመስገን !! አምላከ አረጋዊ ፈቅዶ እና ወዶ ሺዎች ይጠራሉ የተፈቀደላቸው እና የመርጥካቸው ግን ይገኛሉ እና እጅግ ውብ እና ድንቅ በሆነ መልኩ የልማት ፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ ምርቃት ስነ-ስርዓት ጥቅምት 20-2015 ዓ-ም በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል ተካሔደ!!
ምስጋና
ሁሌም አብርነትዎ የማይለየን በጠራንዎ ቦታ ሁሉ ጊዜዎትን አጣበው የሚገኙልን በቡራኬዎት በጸሎትዎ ከጐናችን የቆሙልን የፕሮጀታችንን አላማ ጠልቀው የተረዱልን ለክቡር አባታችን የለሚ ኩራ እና የካ ክ/ከተማ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ መላከ ምህረት ዘካርያስ አዱኛ ላሳዩን ትልቅ አብሮነት እና ብርታታችን ስለሆኑልን እና በቀጣይም አብረውን ስለሚሆኑ አምላከ አረጋዊ ይስጥልን!!
ለደብራችን አስተዳዳሪ እርሶን ያለ ቅን ልብ ያለው ለለውጥ ለስራ የሚተኩ የሰከኑ አባት የሚችሉትን ብቻ ሳይሆን የማይቻልዎትንም የሚጥሩ አባታችን መላከ ሰላም መኮንን ደጀኔ ፣ እንዲሁም ስራን ማሳደር የማይወዱት ነገር ቀለል አድርገው የሚረዱት ትጉህ የስራ ሰው የደብራችን ጸሀፊ ክቡር ቀስስ እና መምህር ዬሴፍ ፣ አጠቃላይ የሰበካ ጉባኤው አባላት ፣አቶ እስክንድር ከአባልነትም በላይ ካለው ቀንሶ እየሰጠ ለማሳካታችን ትልቁን ፍርሻ ትወስዳለህ ፣ አቶ እንዳለ በቀናነት ነገሮችን መፍትሄ በመስጠት ለመሳካቱ የአንበሳውን ድርሻውን ስለተወጡልን፣ መሪጌታ ኪነጥበብ ቄስ ዘላለም እና ሌሎቻችሁም ሁሉ በጻድቁ ስም እናመሰግናለን ፣ የደብራችን ህንጻ ኮሚቴዎች ሁላችሁም ከልብ ከልብ በጻድቁ ስም እናመሰግናለ፣
የማህበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል የሽያጭ ማእከላቱን ስለፈቀደልን እናመሰግናለን!!
የካ ደሳለኝ መዝሙር ቤት፣ ቦሌ መድሀሃኒአለም ጌቴሰማኔ ንዋይ ቅዱሳት መሸጫ ፣ ኡራኤል ቤ/ክ ህንጻው ስር የንዋየት ቅዱሳት መሸጫ፣ እስጢፋኖስ ቃለ አብ መጽሀፍት መሸጫ መደብር፣ ከልብ በጻድቁ ስም እናመሰግናለን!!
የደብራችን ካህናት እና ዲያቆናት፣ የቢሮ ሰራተኞች፣ ትኬቶችን በመሸጥ ለምእመናን የፕሮጀክቱን አላማ በማስረዳት ሰፊ ስራ ስለሰራችሁልን እና ከዚህም በኋላ አብራችሁን ስለምትሰሩ በጻድቁ ስም እናመሰግናለን!!
የሰንበት ት/ቤቱ በአገልግሎቱ አብሮን ስለነበር እናመሰግናለን!!
የአካባቢ ወጣቶች ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ እስከምሽት እየቆያችሁ ለዚህ ውጥን ስኬት ላበረከታችሁት አስተዋጽኦ በጻድቁ ስም እናመሰግናለን!!
ሚዲያ:-
ኢቲ አርት ሚዲያ ከማስታወቂያ ስራው ጀምሮ በቦታው ላይ በመገኘት በቀጥታ ስርጭት ለአለም እንድንደርስ ስላረጋችሁልን እና የልማቱ አጋር በመሆን አብራችሁን ስለነበራችሁ በጻድቁ ስም እናመሰግናለን!!
በማስታወቂያ ስራው ላይ የተሳተፋችሁልን አርቲስት ህይወት ጌታሁን ፣ አርቲስት ናዶስ አዳነ፣ አርቲስት ተወዳጅ ቤኩማ፣ አርቲስት ብስራት ገ/ጻድቅን በጻድቁ ስም እናመሰግናለን አብሮነታችሁ አይለየን
በመጨረሻም መጠራታችሁን አውቃችሁ ከልባችሁ መክራችሁ በቦታው ላይ በመገኘት የፕሮጀክታችን አካል ስለሆናችሁ በጻድቁ ስም እናመሰግናለን!!
28/10/2022