06/02/2026
በአዋጁ የተከለከሉት የፕላስቲክ ከረጢቶች የትኞቹ ናቸው?
ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ የፕላስቲክ ከረጢቶችን መጠቀም የሚከለክለው አዋጅ ካሳለፍነው ጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡
ሕብረተሰቡም አዋጁ የወጣበትን ዓላማ በመረዳት የተከለከሉ የፕላስቲክ ከረጢቶችን ባለመጠቀም የበኩሉን ኃላፊነት እየተወጣ ይገኛል፡፡
ይሁን እንጂ በአዋጁ የተከለከሉ የፕላስቲክ ከረጢቶች የትኞቹ ናቸው የሚለው በሕብረተሰቡ ዘንድ ግርታ መፍጠሩን ፋና ዲጂታል ባደረገው ቅኝት ለመረዳት ችሏል፡፡
በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው ባለሱቆች እና ሸማቾች እንደሚሉት÷ ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ የፕላስቲክ ከረጢቶች የሚለው ሃሳብ በተወሰነ መልኩ ግርታን ፈጥሯል፡፡
ስለሆነም የፕላስቲክ ከረጢቶች ማለትም አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ እና መልሶ ዑደት (ሪሳይክል) የሚደረጉትን በተመለከተ ሰፊ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የከተማ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ክትትል ዴስክ ኃላፊ አቶ ዋሲሁን ዓለሙ ለፋና ዲጂታል በሰጡት ማብራሪያ÷ በአዋጁ የተከለከሉት የፕላስቲክ ከረጢቶች በተለምዶ “ፌስታል” ተብለው የሚጠሩት ናቸው፡፡
እነዚህ ፕላስቲኮችም አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ ውለው በቀጥታ የሚወገዱ ሲሆን÷ በመልሶ ዑደትም ጥቅም ላይ እንደማይውሉ አስረድተዋል፡፡
በዚህም መሰረት ክልከላው ኩርቱ በሚል ስያሜ የሚታወቀውን ፌስታል ጨምሮ በተለያየ ዲዛይን የተሰሩና በቀላሉ በስብሰው ከአፈር ጋር የማይዋሃዱ የፕላስቲክ ከረጢቶች ወይም ፌስታሎችን እንደሚያካትት አብራርተዋል፡፡
ከጥር 23 ቀን ጀምሮ ባለው የትግበራ ሒደት ላይ ዳሰሳ መደረጉን ጠቁመው÷ በዚህም ሕብረተሰቡ አዋጁን ለመተግበር ያሳየው ተነሳሽነት የሚበረታታ ነው ብለዋል፡፡
በአተገባበር ሒደቱ ላይ ከግንዛቤ ማነስ ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ውስንነቶችን ለማስተካከል በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም ነው የገለጹት፡፡
ለዚህም መገናኛ ብዙሃንን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻዎች በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ጠቁመው÷ ሕብረተሰቡም የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በሌላ በኩል ከፕላስቲክ ያልተሰሩ የተኪ መያዣዎች ዋጋ ገበያ ላይ ጭማሪ ማሳየቱን ገልጸው÷ ይህም ሁሉም ባለድርሻዎች በቂ ዝግጅት ባለማድረጋቸው የተከሰተ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ከፕላስቲክ ያልተሰሩ የተኪ መያዣዎችን አቅርቦት ለማሳደግ ይሰራል ነው ያሉት፡፡
በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ 1383/2017 መሰረት የፕላስቲክ ከረጢቶችን የተጠቀመ ወይም ለመጠቀም ይዞ የተገኘ ማንኛውም ግለሰብ ከ2 ሺህ ብር የማያንስ ከ5 ሺህ ብር የማይበልጥ የገንዘብ ቅጣት ይጣልበታል፡፡
ኤፍ ኤም ሲ
02/02/2026
የኮልፌ ወረዳ 10*መሀል ቀለበት አስፓልት መንገድ በስዊፐር መኪና ተፀድቷል።
25/05/2018 ዓ/ም
ኮልፌ ወረዳ 10 በዛሬ ዕለት በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ የመሀል ቀለበት አስፓልት መንገድ በስዊፐር መኪና ተፀድቷል።
ወረዳውም በተቀናጀ የፅዳት ስርዓት ከዋና መንገድ እስከ መጋቢና የውስጥ ለውስጥ መንገዶች በስታንዳርዳቸው መሰረት እየተፀዱ መሆናቸው በክትትልና ድጋፍ ተረጋግጧል።
27/01/2026
በወረዳው በሚገኙ የተለያዩ ብሎኮች ለሚገኙ ነዋሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ።
19/05/2018
💫በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ላይም የደንብ ፣ የግንዛቤ ፣ የደረቅ ቆሻሻ ፣ የመልሶ ባለሙያዎች በመገኘት በተቀናጀ መልኩ ግንዛቤ መስጠት የተቻለ ሲሆን የደረቅ ቆሻሻ አለያየት አወጋገድና ብሎክን ፅዱና ውብ ማድረግ ላይ ግንዛቤ መስጠት ተችሏል።
ከዚህ በተያያዘም በብሎክ ደረጃ ደስትቢን ለማስተከልና ብሎኮቹን ሞዴል ለማድረግ ከነዋሪው ጋር መግባባት ላይ መድረስ መቻሉ ተገልጿል።
በመጨረሻም የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ፍሬያማና ውጤታማ ሆኖ አልፏል።
22/01/2026
ተቋማትን ውብ፣ ፅዱና ማራኪ በማድረግ ዘመናዊ አገልግሎት መስጠት ለተሻለ ውጤት እንደሚያበቃ ተገለፀ
14/05/2018 ዓ/ም
በኮ/ቀ/ክ/ከ/ወረዳ 10 ፅዳትና ውበት አስተዳደር ፅ/ቤት የደረቅ ቆሻሻ አገልግሎት አሰጣጥ እና ግብዓት አስተዳደር ቡድን ስር የሚገኘው ብርሃኑ መኮንንና ጓደኞቻቸው የቤት ለቤት ደረቅ ቆሻሻ መሰብሰብ ህ/ሽ/ማህበር ጊዜያዊ ደረቅ ቆሻሻ ማቆያ ጣቢያ የማስዋብ የማዘመንና ለአገልግሎት ምቹ የማድረግ ስራ ተሰራ፡፡
የፅ/ቤቱ ደረቅ ቆሻሻ አገልግሎት አሰጣጥ እና ግብዓት አስተዳደር ቡድን መሪ ሆኑት አቶ ተክለብርሃን ወሉ እንደገለፁት ከሆነ ፅ/ቤቱ በሚሰራቸው በርካታ ተግባራት ግንባር ቀደም በመሆንና የወረዳውን አካባቢ ፅዱና ማራኪ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሆነ ገልፀው ህብረት ሽርክና ማህበሩ የሚሰጠውን አገልግሎት በመከታተልና የተለያየ ድጋፍ በማድረግ ቤት ለቤት በሚደረገው የደረቅ ቆሻሻ ከመለየት እስከ መሰብሰብ ድረስ ያለውን ሂደት በተለያየ የቁጥጥርና ክትትል ድጋፍ በማድረግ የተሻለ ለውጥ ማምጣት መቻሉን ገልፀዋል፡፡
ህበረት ሽርክና ማህበሩ ለአካባቢው ፅዳትና ውበት መሳለጥ ከሚያበረክተው አስተዋፅዖ በተጨማሪ ጊዜያዊ የቆሻሻ ማቆያ ጣቢያውን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ውብ ፅዱና ማራኪ የማድረግ ስራ ሰርቷል፡፡ በዚህም የማቆያ ጣቢያዉን አጥር በማደስ የተሰበሰበው ቆሻሻ ከጊቢው አልፎ ማህበረሰቡን እንዳይበክል ማድረግ የተቻለ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የደህንነት ካሜራ በመግጠም የዘመነ አገልግሎት እንዲዳብር የማድረግ ስራ መሰራቱ ማየት ተችሏል፡፡
ማህበሩ ከ43 በላይ አባላት ያሉት ሲሆን ወረዳው ላይ ባሉት 7 ቀጠናና 43 ብሎኮች በየቀኑ ጠዋት መዘዋወር ከንግድ ተቋማትና ከሁሉም ብሎኮች የዞኒንግ ስራ የሚሰሩ ሲሆን ወረዳው ላይ ላሉ 6571 አባወራና እማወራ በሳምንት ሁለት ጊዜና ከዛ በላይ በስታንዳርዱ መሰረት የቤት ለቤት የደረቅ ቆሻሻ መሰብበሰብ አገልግሎት እንደሚሰጡ ከፅ/ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
ምንጭ :- የወረዳ 10 ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት
17/01/2026
የከተራና የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ የፅዳት ንቅናቄ ተደረገ
09/05/2018 ዓም
የኮ/ቀ/ክ/ከ/ወረዳ 10 ፅዳትና ውበት አስተዳደር ፅ/ቤት
በኮ/ቀ/ክ/ከ/ወረዳ 10 አስተዳደር የጥምቀት በዓልን በፅዱ አዲስ አበባ በሚል መሪ ቃል የከተራና የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ገዳም ጊቢ ውሰጥ የፅዳት ንቅናቄ ተደረገ፡፡
በፅዳት ንቅናቄው ላይ የክፍለ ከተማው ህዳሴ ግድብ ማ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ምስጋናው፣ የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቃሲም ሱሩርና የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ደስታው ካሳውን ጨምሮ ፅዳትና ውበት ፅ/ቤት ኃለፊ አቶ ያሬድ ሽፈራውና ሌሎች አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉ ሲሆን የፅዳት ዘመቻው ሃይማኖታዊና ሃገር አቀፍ የሆኑ በዓላትን መንግስት በሁሉም ዘርፎች ድጋፍ በማድረግ እንደሚያከናውን ማሳያ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
የከተራና ጥምቀት በዓል ከማይዳሰሱ ቅርሶች መካከል አንዱ እንደመሆኑና የቱሪስት መስህብ በመሆኑ ትኩረት የሚሰጠውና ከሃይማኖቱ ተከታዮች በተጨማሪ የሁሉም ኢትዮጵያዊ በዓል እንደሆነ የገለፁት የክፍለ ከተማው ህዳሴ ግድብ ማ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ምስጋናው በአሉን በፅዱ አዲስ አበባ ለማክበር የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መፍጠር ከሁሉም ማህበረሰብ የሚጠበቅ ግዴታ እንደሆነም አክለው ገልፀዋል።
አካባቢያችንን በማፅዳት ፅዱና ውብ አዲስ አበባን መፍጠር የሁላችንም ግዴታ ነው ያሉት አቶ ቃሲም ሱሩር በአላት የእርስ በእርስ ትስስራችን የሚጠናከርባቸውና የአብሮነት መንፈስን የሚያላብሱ በመሆናቸው እንደዚህ ባለ ተግባር በጋራ ልናከብራቸው ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ምንጭ :-የኮ/ቀ/ክ/ከ/ወረዳ 10 ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት
15/01/2026
"የጥምቀት በዓልን በፅዱ አዲስ አበባ'' በሚል መሪ ቃል ውይይት ተካሄደ።
ቀን 07/05/2018ዓ.ም
በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 ጽዳትና ውበት አስተዳደር ጽ/ቤት በዛሬው ዕለት የጥምቀትና የከተራ በዓልን ምክንያት በማድረግ ''የጥምቀት በዓልን በፅዱ አዲስ አበባ''በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው እቅድ ኦረንቴሽን የክ/ከተማ ደጋፊ ባለሙያዎች፣የጽ/ቤቱ ኃላፊ፣ቡድን መሪዎች እንዲሁም ሁሉም ባለሙያዎች በተገኙበት የጋራ ተደርጓል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
➜➜ የጥምቀት በዓልን በፅዱ አዲስ አበባ
➪➩ ቆሻሻ መጣል ይብቃ!!
➪➩ሁሉም አካባ ቢውን የማፅዳትና የማስዋብ ግዴታ አለበት!
የወረዳ 10 ፅዳትና ውበት አስተዳደር ጽ/ቤት
12/01/2026
የወርቃማ ሰኞ ውይይት ተካሄደ።
ቀን 04/05/2018
በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፅዳት እና ውበት አስተዳደር ጽ/ቤት በዛሬው ዕለት የጽ/ቤት ኃላፊ፣ስራ ሂደቶች እና ሁሉም የጽ/ቤት ባለሙያዎች በጋራ በመሆን የወርቃማ ሰኞ ውይይት ተደርጓል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ወረዳ 10 ጽዳት እና ውበት አስተዳደር ጽ/ቤት
03/01/2026
ሳምንታዊ የፅዳት ዘመቻ በወረዳው በሚገኙ ብሎኮች ተካሄደ።
ኮልፌ ወረዳ 10 ፅዳት እና ውበት አስተዳደር ጽ/ቤት
ቀን 25/04/2018
በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፅዳት እና ውበት አስተዳደር ጽ/ቤት ዛሬ የጽ/ቤት ባለሙያዎችና ስራ ሂደቶች በጋራ በመሆን ሳምንታዊ የብሎኮች የፅዳት ዘመቻ ህብረተሰቡን በመቀስቀስ ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ ሁሉንም ብሎኮች የማፀዳት ስራ ተሰርቷል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
➪➩ ቆሻሻ መጣል ይብቃ!!
➪➩ሁሉም አካባ ቢውን የማፅዳትና የማስዋብ ግዴታ አለበት!!
➡️ ሳምንታዊ ብሎክ ለብሎክ ፅዳት ሁላችንም ወጥተን የማፅዳት ግዴታ አለብን !!
➡️ አከባቢያችንን ውብ እና ፅዱ ማራኪ አድርገን ለትውልድ የማሰተላለፍ ግዴታ አለብን!!
➮➩ ፅዳት የስልጣኔ መገለጫ ነው
ወረዳ 10 ጽዳት እና ውበት አስተዳደር ጽ/ቤት
02/01/2026
,ሳሞንታዊ የትምህርት ቤቶች የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ።
በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፅዳት እና ውበት አስተዳደር ጽ/ቤት ዛሬ በቀን 24/04/2018 የጽ/ቤት ባለሙያዎችና ስራ ሂደቶች በጋራ በመሆን ሳምንታዊ የት/ቤቶች የፅዳት ዘመቻ ተማሪዎችን፣መምህራንን እና የአስተዳደር ሰራተኞችን በማስተባበር የማፀዳት ስራ ተሰርቷል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
➪➩ ቆሻሻ መጣል ይብቃ!!
➪➩ት/ቤታችንን በማፅዳት ንፁህ አካባቢ ላይ እንማር
➮➩ ፅዳት የስልጣኔ መገለጫ ነው
"ዛሬን የተሻለ በማድረግ ነገን የሚናፍቅ ትውልድ እንፍጠር"
ወረዳ 10 ጽዳት እና ውበት አስተዳደር ጽ/ቤት
01/01/2026
የኮልፌ ወረዳ 10 የቅብብሎሽ ጣቢያ ዘመናዊ ካሜራ አስገጠመ።
ኮልፌ ወረዳ 10 ፅዳትና ውበት አስተዳደር ፅ/ቤት
የኮልፌ ወረዳ 10 የቅብብሎሽ ጣቢያ የጀመረውን የሪፎርም ስራዎች በማጠናከር ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየሰራ እንደሚገኝ ተገለፀ።
ከተሰሩት የሪፎርም ስራዎች ውስጥ በዋነኛነት ዘመናዊ ካሜራ ማስገጠም የተቻለ ሲሆን የሰራተኛውን የስራ ላይ ደህንነትና መሰል ስራውን ለማሳለጥ የሚያግዙ ተግባራትን የሚሰራው የዘመናዊ ካሜራ መገጠሙን ተገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪም ምድረ ግቢን በማስዋብ ሂደት ቅጥር ጊቢውን በኤጋ ቆርቆሮ የታጠረ ሲሆን በኮሊደር ልማት ስታንዳርድ በቀለም ቅብ ማልማትን ጨምሮ የግቢውን 20 በ50 ራድየስ የማስዋብ ስራ የተሰራ ሲሆን አጠቃላይ ስራዎቹም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።
30/12/2025
የቀለበት መንገድ አስፓልት አካፋይ በስዊፐር ማሽን የጊዜ ሰሌዳውን ጠብቆ እየተፀዳ መሆኑተገለፀ።
ቀን 21/04/2018
,ኮልፌ ወረዳ 10 ፅዳትና ውበት አስተዳደር ፅ/ቤት
በኮልፌ ወረዳ 10 ከ18 ጀምሮ እስከ ሆላንድ ኤምባሪ የሚደርሰው የቀለበት መንገድ አስፓልት አካፋይ በስዊፐር ማሽን እየተፀዳ መሆኑ ተገለፀ።