08/07/2025
በንፁሀን ደም የሚሳለቁ ሁለት ሀይማኖት የለሽ ግለሰቦች
የእSራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ሴጣንያሁ ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኖቤል የሰላም ሽልማት እጩ ደብዳቤ አቀረቡ። ትራምፕ በተናጥል በጋዛ በእስራኤል ወታደሮች ላይ የተፈጸመውን አስከፊ ጥቃት ሪፖርቶችን አረጋግጠዋል።
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ወቅታዊ Page, School, Addis Ababa �, Addis Ababa.
08/07/2025
በንፁሀን ደም የሚሳለቁ ሁለት ሀይማኖት የለሽ ግለሰቦች
የእSራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ሴጣንያሁ ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኖቤል የሰላም ሽልማት እጩ ደብዳቤ አቀረቡ። ትራምፕ በተናጥል በጋዛ በእስራኤል ወታደሮች ላይ የተፈጸመውን አስከፊ ጥቃት ሪፖርቶችን አረጋግጠዋል።
23/05/2025
እናቷም የእንጀራ አባቷም በሞት እንዲቀጡ ተወሰነI ወላጅ እናት ወ/ሮ ሀና በየነ ትባላለች የድሬዳዋ ከተማ ገንደቆሬ ሰፈር ነዋሪ ስትሆን ከቀድሞ ባሏ ጋር የተፈታችው ይህቺ ሴት ከእሷ ጋር እየኖረ ባለው ሌላ ወንድ ከአብራኳ የወጣችውን የገዛ ሴት ልጅዋ ተገዳ መደፈሯን ስታውቅ እጮኛዋን በወንጀል እንዲቀጣ ማድረግ ሲገባት የ11 ዓመት ልጇ ላይ ፈርዳ መረጃ ለማድበስበስ በማሰብ ልጇን ላይ ጫና በመፍጠር በድብደባ አካላዊ ጉዳት ከማድረስ በተጨማሪ ከ5ተኛ ክፍል የትምህርት ገበታ እና ከጎረቤቶቿ በመነጠል ከማንም ሰው ጋር ምንም ግንኙነት እንዳታረግ በማድረግ ለብዙ ጊዜ ቤት ተዘግቶባት እና ስራ ቦታ ድረስ ከስሯ ሳትነጥላት ብትንቀሳቀስም መረጃ ለመደበቅ በቂ ሆኖ ስላላገኘችው በመጨረሻ በአብራኳ በወጣችው የገዛ ልጇ ላይ የሰራችው ተደጋጋሚ የአረመኔ ሥራ ሳያንሳት እጮኛዋን ከወንጀል ለማትረፍ መረጃ ለማጥፋት ህዳር 1 ቀን 2015 ዓም ከእጮኛዋ ጋር በመተባበር ቀጥቅጠው ህፃን በአምላክ ግርማን ገደሏት።
***
በወላጅ እናቷ እና እንጀራ አባቷ ሕይወቷ ያለፈው ሕፃን በአምላክ ግርማ አበጋዝ ጉዳይ ዛሬ ግንቦት 15 ቀን 2017 ዓ.ም የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት የቅጣት ውሣኔ ሰጥቷል።
ተከሳሾቹም
እናቷ ሀና በየነ በሞት እንድትቀጣ ተወስኗል::
እንጀራ አባቷ ብሩክ በሞት እንዲቀጣ ተወስኗል::
#ችሎት
26/04/2025
አርሰናል ለባርሴሎናው ተከላካይ ኩንዲ 55M€ አቀረበች
26/04/2025
ተወዳጁ ማስተር አብነት በቲክቶክ 4M ተከታይ በማፍራት የመጀመሪያው ኢትዮጲያዊ ሆኗል
ፍቅራችሁን ግለፁለት
26/04/2025
የሩሲያ የጦር አውሮፕላን ወደ ኔቶ አባል ሃገር ጥሶ ሊገባ ሲል የኔቶ ተዋጊ ጀቶች ተረባርበው ማስመለሳቸው ተዘግቧል።
ሩሲያ የላከችው የጦር አውሮፕላን ተራ የጦር አውሮፕላን ሳይሆን ለኒውክለር ጥቃት ጠቃሚ መረጃዎችን የሚሰበስብ ኢሊውዥን የተባለው IL-20 መሆኑ ታውቋል።
ከሰሞኑ የኔቶ በር ደጋግሞ እያንኳኳ ያለው የሩሲያ አየር ሃይል በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ ለሶስተኛ ግዜ የኔቶ አየር ክልል ጥሶ ለመግባት መሞከሩን የኔቶ አባል ሃገሯ ስዊድን ጦር አሳውቋል።
በኔቶ ትዕዛዝ ስር የነበሩ ሁለት የስዊድን ተዋጊ ጄቶች ትላንት ሀሙስ ምሽቱን በባልቲክ ባህር ላይ ወደ ፖላንድ አየር ክልል ሰብሮ ለመግባት እየተቃረበ የነበረን የሩሲያ አደገኛ የስለላ አውሮፕላን ማስመለሳቸውን የስዊድን የጦር ሃይሎች አስታውቋል።
በጁምዓ ቀን ሱረቱል ካህፍን የቀራ ሰው ስምንት ቀን ይጠበቃል
ደጃል ቢወጣ እንኳን ከሱ ይተርፋል
ረሱል صل الله عليه وسلم
25/04/2025
ነብስ ይማር
የኢትዮጵያ ዶክተሮች -
1. 7 ዓመት ለፍቶ ተምሮ በዛች አንዳንዶች በቀን በሚያጠፉት ደሞዝ ተቀጥሮ ያስተማረውን ህብረተሰብ ያገለግላል::
2. ለራሱ ሳይሆን ይኖራል::
3. አንዳንዴም ደሞ እንደዚህ በግፍ ይሞታል::
ዶ/ር ገ/ሚካኤል ወ/መልዓክ ይባላል።
በ2015 ዓ.ም ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተመረቀ ወጣት
ሐኪም ነበር።
በአማራ ክልል እናት ሆስፒታል ተቀጥሮ ያስተማረውን ህብረተሰብ ያገለግላልም ነበር።
ነገር ግን ትላንትና ረፋድ ላይ ወደቤተሰቦቹ እየሄደ ባለበት ሰዓት ባልታወቁ ሰዎች ከመኪና ውስጥ በጥይት ተመትቶ ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል።
Via Wolkite university medical Students.
#የኢትዮጵያዶክተሮች
24/04/2025
በሻሸመኔ ከተማ ሶስት የቁርአን ሀፊዝ የነበሩ ወጣቶች በድንገተኛ አደጋ ወደ አኼራ መሻገራቸው ተሰማ!
በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ከተማ ሶስት የቁርአን ሀፊዝ የነበሩ ወጣቶችን በድንገተኛ የመኪና አደጋ በትላንትናው ዕለት ወደ አኼራ መሻገራቸው ተሰምቷል።
ወጣቶች በቱርክ ሀገር የትምህርት እድል አግኝተው ፎርም ለመሙላት ከሻሸመኔ ከተማ በመነሳት ወደ አዲስአበባ በሚጓዙበት ሰአት ነገሌ ሲደርሱ ይጓዙበት የነበረው መኪና ከቦቲ መኪና ጋር ተጋጭቶ ህይወታቸው እንዳለፈ ተገልጿል።
ሳዳም ቡሊ፣ ኢስማኤል አብደላ እና ወንድሙ አባባ የተባሉት ወጣቶቹ ሶስቱም የቁርአን ሀፊዝ የነበሩና በሻሸመኔ ከተማ በሚያደርጉት ኢስላማዊ እንቅስቃሴ የታወቁ እንደነበሩ ተገልጿል።
የወጣቶች ስርዓተ ቀብር በዛሬው ዕለት በርካታ የሻሸመኔ ከተማ ነዋሪዎች ኡለማኦችና ወጣቶች በተገኙበት በሻሸመኔ ከተማ የሙስሊም መካነ መቃብር ተፈፅሟል።
- በድንገተኛ አደጋ ላጣናቸው ወጣቶች አላህ ማረፊያቸውን ጀነት እንዲያደርግላቸው ሚዲያችን እየተመኘ፤ ለመላው ወዳጆቻቸውና ቤተሰቦቻቸው ሶብርንና መፅናናትን ይመኛል።
17/04/2025
የሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ አንቾሎቲ ከ April 26 ቱ ኮፖ ድላሬይ ከ ባርሳ ጋር ካለው ጨዋታ በኃላ ይሰናበታሉ ተባለ