Bethlehem youth academy

Bethlehem youth academy

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Bethlehem youth academy, School, Addis Ababa.

Photos from Bethlehem youth academy's post 28/03/2026

ቀን፦ ሀሙስ፣ መጋቢት 18፣ 2018 ዓ.ም

ለተወደደችሁ የቤተልሔም ዩዝ አካዳሚ የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪ ወላጆች በሙሉ፦

​በመጀመሪያ ለልጆቻችሁ የትምህርት ስኬት የምታደርጉትን ያልተቆጠበ ድጋፍ እያመሰገንን የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ (ሚኒስትሪ) ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎቻችን ለፈተናው በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ፣ በራስ መተማመናቸው እንዲጎለብትና አስፈላጊው የስነ-ልቦና ዝግጅት እንዲኖራቸው የሚያግዝ ልዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በዛሬው ዕለት መሰጠቱን በደስታ እንገልጻለን።

​ትምህርት ቤታችን ካለው የተማሪዎች ውጤታማነት ራዕይ በመነሳት ከዚህ ቀደምም ተማሪዎቻችን ራሳቸውን ለከተማ አቀፍ ፈተና ዝግጁ እንዲያደርጉ የሚያስችሉ ተከታታይ ስልጠናዎች በትምህርት ቤቱ አስተዳደር በኩል ሲሰጣቸው መቆየቱ ይታወሳል። የዛሬው ስልጠናም የዚሁ ቀጣይነት አካል ሲሆን ውጤታማ ተማሪዎችን በማፍራት የረጅም ዓመት ልምድ ባለው በመምህር ናሆም ፍቅሩ አማካኝነት የቀረቡት ዓበይት ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦

1. ​የዕድገት አስተሳሰብ (Growth Mindset) ግንባታ፦ ተማሪዎች ተግዳሮቶችን የመጋፈጥ፣ ጥረት ወደ ስኬት እንደሚመራ የማመን እና "አንጎል እንደ ጡንቻ ነው - ብዙ በተጠቀምንበት መጠን እየጠነከረ ይሄዳል" የሚለውን ጽንሰ-ሐሳብ እንዲረዱ ተደርጓል።
2. የግብ መተለምና የማቀድ ክህሎት (SMART Goals)፦ በቀሩት ጥቂት ወራት ሊተገብሯቸው የሚገቡ ግልጽ፣ ሊለኩ የሚችሉና በጊዜ የተገደቡ ግቦችን በማውጣት ለውጤት መስራት እንደሚገባቸው ስልጠና ተሰጥቷል።
3. ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም (Eisenhower Matrix)፦ ተግባራትን እንደ አስፈላጊነታቸውና አስቸኳይነታቸው ቅደም ተከተል በማስያዝ፣ መዘናጋትን በማስወገድ ጊዜን በአግባቡ ስለመጠቀም ተመክረዋል።
4. ውጤታማ የአጠናን ስልቶች፦ የፖሞዶሮ ቴክኒክ (በጥናት መሃል ዕረፍት መውሰድ)፣ አጫጭር ማስታወሻዎችን ማዘጋጀትና ጽንሰ-ሐሳቦችን በጥልቀት የመረዳት (Conceptualization) ዘዴዎች በዝርዝር ቀርበዋል።
5. የፈተና አሰራር ስልቶች (Exam-Taking Strategies)፦ ትዕዛዛትን በጥንቃቄ ማንበብ፣ የሰዓት አጠቃቀም እና ለከባባድ የምርጫ ጥያቄዎች የማስወገድ ዘዴን (Elimination techniques) ስለመጠቀም ተግባራዊ ምክረ-ሐሳቦች ተሰጥተዋል።

ስልጠናው በዚህ ብቻ የሚያበቃ ሳይሆን በቀጣይም ተማሪዎቻችን የዝግጅት አቅማቸውን የሚያሳድጉበት፣ ፈተናውን በብቃት በመስራት የላቀ ውጤት ባለቤት እንዲሆኑ የሚረዳ ተጨማሪ ስልጠና የሚሰጣቸው መሆኑን በደስታ እንገልጻለን።

​ይሁን እንጂ ፈተናው ከመቼውም ጊዜ በላይ እየቀረበ በመሆኑ በቀሩት ጥቂት ወራት ልጆቻችሁ በቤት ውስጥ ከመቼውም ጊዜ በተለየ ሁኔታ ልዩ ትኩረትና ድጋፍ እንድታደርጉላቸው በአፅንዖት እናሳስባለን። በተለይም በዚህ ወሳኝ ወቅት ተማሪዎች ትኩረታቸውን ከሚበታትኑ እንደ ማህበራዊ ሚዲያ (Facebook, TikTok, YouTube ወዘተ) አጠቃቀም፣ ከልክ ያለፈ ጨዋታና ፊልም ከማየት ራሳቸውን እንዲያርቁ እና ጊዜያቸውን ሙሉ በሙሉ ለጥናት እንዲያውሉ በቅርበትና በጥብቅ እንድትከታተሏቸው በአክብሮት እንጠይቃለን።

በመጨረሻም ​ልጆቻችን በስልጠናው ያገኟቸውን ፅንሰ-ሐሳቦች በተግባር እንዲያውሉና ለታላቅ ስኬት እንዲበቁ የእናንተ የቤት ውስጥ ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን በድጋሚ እናሳስባለን።

​ከሰላምታ ጋር!
የትምህርት ቤቱ አስተዳደር

ለመልካም ሥነ-ምግባርና ለትምህርት ጥራት እንተጋለን!
We Strive for Virtue and Quality of Education!

Photos from Bethlehem youth academy's post 27/03/2026

ቀን፦ ሀሙስ፣ መጋቢት 17፣ 2018 ዓ.ም

ለተወደደችሁ ቤተልሔም ዩዝ አካዳሚ የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪ ወላጆች በሙሉ፦

​በመጀመሪያ ለልጆቻችሁ ትምህርታዊ ስኬት የምታደርጉትን ያልተቆጠበ ድጋፍ እያመሰገንን የ6ኛ ክፍል የከተማ አቀፍ (ሚኒስትሪ) ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎቻችን ለፈተናው በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉና በራስ መተማመናቸው እንዲጎለብት፣ በቂ የስነ ልቦና ዝግጅት እንዲኖራቸው የሚያግዝ ልዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በዛሬው ዕለት ተሰጥቷል።

​ይህ ስልጠና ተማሪዎችን፣ መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞችን በማሰልጠን እና ውጤታማ እንዲሆኑ በማድረግ የረጂም ዓመት የካበተ ልምድ ባለው በመምህር ናሆም ፍቅሩ አማካኝነት ሲሆን ተማሪዎቻችን በፈተና ወቅት ሊከተሏቸው በሚገቡ የፈተና አስራር ስልቶችና የአጠናን ዘዴዎች ላይ ትኩረት በማድረግ በቀሩት ጥቂት ወራት ራሳቸውን ለከተማ አቀፍ ፈተናው በበቂ ሁኔታ ዝግጁ እንዲሆኑ የሚያስችል እንደሆነ እናምናለን። በዛሬው የስልጠና መድረክ በዋናነት የተነሱ ዓበይት ርዕሰ ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው፦

1. ​የዕድገት አስተሳሰብ (Growth Mindset) ግንባታ፦ ተፈታኝ ተማሪዎችችን ተግዳሮቶችን የመጋፈጥ፣ ከውድቀት የመማር እና ጥረት ወደ ስኬት እንደሚመራ የማመን አስፈላጊነት።
2. የግብ መተለምና የማቀድ ክህሎት (SMART Goals)፦ በቀሩት ጥቂት ወራት ተፈታኝ ተማሪዎቻችን ሊተገብሯቸው የሚገቡ ግልጽ፣ ሊለኩ የሚችሉ እና በጊዜ የተገደቡ ግቦችን በማውጣት ለውጤት መሥራት።
3. ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም፦ ተፈታኝ ተማሪዎቻችን በቀሩት ጥቂት ወራት ሊተገብራቸው የሚገቡ የጥናት መርሐግብር ማውጣት፣ ተግባራትን ቅደም ተከተል ማስያዝ (Eisenhower Matrix) እና መዘናጋትን ማስወገድ።
4. ውጤታማ የአጠናን ስልቶች፦ ተማሪዎቻችን አጫጭር ማስታወሻዎችን በአግባቡ በአግባቡ ማዘጋጃት እና መጠቀም፣ የፖሞዶሮ ቴክኒክ (በጥናት መሃል ዕረፍት መውሰድ) እና ጽንሰ-ሐሳቦችን በጥልቀት የመረዳት (Conceptualization) ዘዴዎች።
5. የፈተና አሰራር ስልቶች (Exam-Taking Strategies)፦ ተፈታኝ ተማሪዎቻችን ትዕዛዛትን በጥንቃቄ ማንበብ፣ የሰዓት አጠቃቀም፣ በስሌት መመለስ እና ለከባባድ የምርጫ ጥያቄዎች የማስወገድ ዘዴን (Elimination techniques) መጠቀም።

​ በዛሬው ዕለት ለ6ኛ ክፍል ተማሪዎች የተሰጠው ስልጠና በቀሪው አጭር ጊዜ ውስጥ ራሳቸውን በከተማ አቀፍ ደረጃ ለሚሰጠው ፈተና ራሳቸውን በበቂ ሁኔታ እንዲያዘጋጁ ትልቅ እገዛ ያደርጋል ብለን እናምናለን።

በመጨረሻም ልጆቻችን በስልጠናው ያገኟቸውን ዓበይት ፅንስ ሀሳቦች በተግባር እንዲያውሉ በቤት ውስጥም አስፈላጊና ተገቢነት ያለው ክትትልና ድጋፍ በቋሚነት እንድታደርጉላቸው በአክብሮት እንጠይቃለን። በነገው ዕለትም ለ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ተመሳሳይ ስልጠና የሚሰጥ መሆኑን ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን።

​ከሰላምታ ጋር!
​የትምህርት ቤቱ አስተዳደር

ለመልካም ሥነ ምግባርና ለትምህርት ጥራት እንተጋለን!
We Strive for Virtue and Quality of Education!

25/03/2026

ቀን፦ መጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ.ም

የምስጋና መልዕክት ለመቄዶንያ አለኝታ ለሆናችሁ የቤተልሔም ዩዝ አካዳሚ ቤተሰቦች በሙሉ
ሁሌም ኩራታችን ናችሁ! የቤተልሔም ዩዝ አካዳሚ ማህበረሰብ በሙሉ የበጎነት እና የርህራሄ ተምሳሌት መሆኑን በዛሬው ምሽት አስመስክሯል !

ለመላው የቤተልሔም ዩዝ አካዳሚ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ ወላጆች እና የአስተዳደር ሠራተኞች በሙሉ፦

​በዛሬው ዕለት ለመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአእምሮ ህሙማን መረዳጃ ማህበርን ለማገዝ በተዘጋጀው የቀጥታ ስርጭት የገቢ ማሰባሰቢያ (Live Fundraising) መርሃ-ግብር ላይ ሁሉም የቤተልሔም ዩዝ አካዳሚ ቤተሰቦች ላሳያችሁት ወደር የለሽ ተሳትፎ እና የደግነት ተግባር ተቋማችን የላቀ ምስጋናውን ያቀርባል።

​ሰው ለሰው መድረስ ካለበት የሰብአዊነት ልክ በላይ በነቃ ተሳትፎአችሁ እና በከበረ ልግስናችሁ ለወገን አለኝታነታችሁን በተግባር አሳይታችኋል። በተለይም ተማሪዎቻችን ገና በለጋ እድሜያችሁ ለችግረኞች የምታዝኑ፣ ለተቸገሩት የምትቆረቆሩ እና የበጎነትን ትርጉም በሚገባ የተረዳችሁ መሆናችሁን ስናይ በትምህርት ቤታችን ስም ትልቅ ኩራት ተሰምቶናል።

​ይህ በዛሬው ዕለት የፈጸማችሁት ተግባር ለተቋማችን ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም አርአያ የሚሆን፣ "ሰው በመሆን ለሰው መድረስ" ምን ያህል ትልቅ ዋጋ እንዳለው ያስመሰከረ ታላቅ የታሪክ አጋጣሚ ነው።

​የቤተልሔም ዩዝ አካዳሚ ማህበረሰብ ሁሌም በእውቀት ብቻ ሳይሆን በስነ-ምግባር እና በበጎነት የታነጸ ትውልድ ለማፍራት እየሰራ ያለ ተቋም መሆኑን ዳግም አረጋግጣችኋል። ለዚህ የተቀደሰ ዓላማ ስኬት ከልብ የመነጨ ጊዜያችሁን፣ ጉልበታችሁን እና ገንዘባችሁን የሰጣችሁ በሙሉ ፈጣሪ በጎነታችሁን ይቁጠርላችሁ እያልን፤ በቀጣይም እንዲህ ባሉ ሰብአዊ ተግባራት ላይ ሁሌም ቀዳሚ በመሆን ያላችሁን አጋርነት ያለማቋረጥ እንድትቀጥሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
​በድጋሚ ለሁላችሁም ምስጋናችን ይድረሳችሁ!
​ ከታላቅ አክብሮት ጋር!
የቤተልሔም ዩዝ አካዳሚ አስተዳደር

ለመልካም ሥነ ምግባርና ለትምህርት ጥራት እንተጋለን!
We Strive for Virtue and Quality of Education!

23/03/2026

Photos from Bethlehem youth academy's post 18/03/2026

Photos from Bethlehem youth academy's post 18/03/2026

Today, students presented creative works made by themselves. In addition, they gave an explanation about one of the internal parts of the human body, the lungs.

11/03/2026

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Address

Addis Ababa