Addis Ababa University Cultural Center

Addis Ababa University Cultural Center

Share

Official account of Addis Ababa University Cultural Center

Celebrating Culture, Creativity & Campus Talent

Events ● Arts ● Culture ● Community

27/05/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች
እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል አድሐ በዓል አደረሳችሁ፣ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የደስታ ይሁንላችሁ ።
ኢድ ሙባረክ

Photos from Addis Ababa University Cultural Center's post 22/05/2026

🎭 “ትዝታ” ምሽት – 56ኛው የአንጋፋ የኪነ-ጥበብ ምሽት

“የአንድ ግጥም አንድ ወግ” አንጋፋ የኪነ-ጥበብ ምሽት ዝግጅት 56ኛው ሳምንት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል።

በዚህ ምሽት በክብር እንግዳነት የተገኙት ታዋቂው ተዋናይ እንግዳሰው ሀብቴ (ቴዲ) በመድረኩ ላይ ተገኝቶ ሙያዊ ልምዱን እና የህይወት ጉዞውን ከታዳሚያን ጋር አካፍሏል። በተጨማሪም የተለያዩ የጥበብ ድግሶች ለታዳሚያን ቀርበዋል።

በ ኮካ ኮላ እና ታምኮን ሶልዩሽንስ ስፖንሰር የተደረገው ይህ ዝግጅት በስኬታማ ሁኔታ ተካሂዶ አልፏል።

✨ በቀጣዩ ረቡዕ በሌላ ልዩ እንግዳ ተሰናድቶ ይጠብቃችኋል።

17/05/2026

🎭 “Tizita” Night – 56th Angafa Art Night

The 56th Angafa Art Night organized by the Addis Ababa University Cultural Center will take place on Wednesday, May 20, 2026, under the theme “Tizita.”

The renowned actor Engidasew Habte will attend as the guest of honor and share his professional journey and experiences with the audience.

The evening will also feature poetry, storytelling, music, monologues, and other artistic performances prepared for our beloved audience.

✨ As always, the night promises creativity, inspiration, and unforgettable moments.

🕦 Time: 11:30 AM
📍 Place: Addis Ababa University Cultural Center Hall

Everyone is warmly invited!

🚪 Note: For literature enthusiasts and attendees who are not currently students of the university, entry will be available through Gate 5.

Photos from Dawit Tsige's post 15/05/2026

ክቡር አርቲስት ዳዊት ፅጌ፣
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል፣ በተማሪዎቻችን እንዲሁም በመላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ስም፤ ይህንን ልብ የሚነካና እጅግ አበረታች የሆነ የምስጋና መልእክትን ስናነብ የተሰማንን ጥልቅ ደስታና ክብር ልንገልጽልህ እንወዳለን።

በ55ኛው የኪነ-ጥበብ (የኔ ዜማ) ምሽት ላይ ጥሪያችንን አክብረህ በእንግድነት ስለተገኘህ ከምሁራን፣ ከተማሪዎቻችን እንዲሁም ከጥበብ አፍቃሪው ጋር ያሳለፉት ጊዜ ለእኛም ሆነ ለተማሪዎቻችን እጅግ ልዩ እና ታሪካዊ ነበር። አንተ በመድረካችን መገኘት በተለይም በኪነ-ጥበብ ዘርፍ ልዩ ተሰጥኦና ፍላጎት ላላቸው ወጣት ተማሪዎቻችን የፈጠረው መነሳሳት እና የሞራል ስንቅ በቀላሉ የሚገመት አይደለም።
በተማሪዎቻችን የፈጠራ ስራዎች (በሙዚቃ፣ ግጥም፣ ትወና፣ ኮሜዲ እና ሌሎችም አቀራረቦች) ላይ የተሰጠን ገንቢ አስተያየት፣ እውቅና እና ያየነው አድናቆት የባህል ማዕከላችን በቀጣይም የሀገራችንን የኪነ-ጥበብ ዘርፍ ወደ ተሻለ ደረጃ የሚያደርሱ ወጣት አቅሞችን ለማውጣትና ለመደገፍ ለሚያደርገው ጥረት ትልቅ ብርታት ነው።
በመልእክተ‍ህ ላነሷቸው የማህበራዊ ሳይንስና ሂዩማኒቲስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ኢዛና አምደወርቅ፣ የባህል ማዕከሉ ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ተስፋዬ እሸቱ፣ እንዲሁም መድረኩን በትጋት ላሳመሩት አስተባባሪዎቻችን፣ የባንዱ አባላት፣ የቴክኒክ ባለሙያዎችና ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ላቀረቡከው ክብር፤ ሁላችንም በጋራ ላንተ ያለንን ከፍ ያለ አክብሮትና ምስጋና እንመልሳለን። ጊዜህን ሰተህ የትውልድ ትስስርን እና የእውቀት ልውውጥን ስላደመክል ከልብ እናመሰግናለን።
በቀጣይም በሌሎች የጥበብ መድረኮች ላይ አብረን እንደምንሰራና የጥበብን ቤተሰብ ይበልጥ እንደምናስተሳስር ሙሉ ተስፋ እያደረግን፣ በሙያ እና በህይወትህ ሁሉ የላቀ ስኬት እንዲገጥምዎ እንመኛለን።
ከላቀ አክብሮት ጋር፣
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል የኮሙኒኬሽን ክፍል
(በተማሪዎችና በሰራተኞች ስም)

Photos from Addis Ababa University Cultural Center's post 15/05/2026

📰 የጥበብ እና የታሪክ ምሽት፡ 55ኛው ሳምንት የአንጋፋ የኪነ-ጥበብ ምሽት ረብዕ ግንቦት 5 ፣2018 ዓ.ም

"የኔ ዜማ ምሽት" | በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል

"የኔ ዜማ" ምሽት በሚል ርዕስ የተዘጋጀው 55ኛው ሳምንት የአንጋፋ የኪነ-ጥበብ ምሽት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፊልም እና ቴአትር ጥበባት ት/ቤ ባህል ማዕከል ከአዳራሽ ውጭ (Outdoor) በተዘጋጀ ማራኪ መድረክ በድምቀት ተካሂዷል። ምሽቱ በሙዚቃ፣ በግጥም፣ በተረት እና ልዩ ልዩ የጥበብ ዝግጅቶች የታጀበ ታሪካዊ ክንውን ነበር።

የዝግጅቱ የክብር እንግዳ እና በወጣቶች ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የሆነው ድምፃዊ ዳዊት ጽጌ፣ ድንቅ የሙዚቃ ዝግጅት ከማቅረቡም ባለፈ የህይወት ተሞክሮውን በማካፈል ለካምፓሱ ተማሪዎች የማይረሳ እና ከፍተኛ መነሳሳትን የፈጠረ ጊዜን አበርክቷል።

በዕለቱ የጥበብ ምሽቱን ለማድመቅ በርካታ የክብር እንግዶች ተገኝተዋል፦
• ዶ/ር ኢዛና አምደወርቅ (የማህበራዊ ሳይንስ፣ ስነ-ጥበባት እና ሂውማኒቲስ ኮሌጅ ዲን)
• ዶ/ር ሽብሩ ተመስገን የተማሪዋች ልማት ማበልፀጊያ ዳይሬክተር
• ወ/ሪት ቤተልሄም (የአ.አ.ዩ የኮሙኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ)
እንዲሁም መምህራን እና ሰራተኞች።

የኦርኬስትራ ኢትዮጵያ የሙዚቃ ባለሙያዎች ያቀረቡት ፕሮፌሽናል የሙዚቃ ዝግጅት ለዕለቱ ድምቀት ልዩ ድርሻ ነበረው።
ከታይም ኮድ (Time Code Events) ጋር በመተባበር የተዘጋጀው የውጭ መድረክ፣ ስክሪን፣ ድምፅ እና መብራት ዝግጅቱን ፍፁም እና የተሟላ አድርጎታል። ይህ ታሪካዊ ምሽት በሰላም እንዲጠናቀቅ ላደረጉት የፌደራል ፖሊስ እና የካምፓስ የጥበቃ አባላት፣ እንዲሁም ላስተባበሩት የባህል ማዕከሉ አባላት በሙሉ ልዩ ምስጋና እናቀርባለን።

🤝 አጋሮቻችን እና ስፖንሰሮች
ለዚህ ዝግጅት መሳካት ድጋፍ ላደረጉልን፦
• ኮካ ኮላ (Coca-Cola)፦ ላደረገው የገንዘብ ስፖንሰርሺፕ።
• ታምኮን ሶሉሽንስ (Tamcon Solutions)፦ ላደረጉልን ተከታታይ ድጋፍ እና ትብብር።
• ዳይናሚክስ ሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን፦ ይህን ታሪካዊ ትዝታ በፎቶ ላስቀሩልን የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
55ኛው ሳምንት የኪነ-ጥበብ ምሽት ትውልድን በማነቃቃት ታሪክ የሰራ ምሽት ሆኖ አልፏል። ከእኛ ጋር ስለነበራችሁ እናመሰግናለን!

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል ኮሚኒኬሽን

14/05/2026

"የኔ ዜማ ምሽት" 🎶 Dawit Tsige brought so much energy and wisdom to Week 55 of Angafa Art Night! Who else was in the crowd? Drop a ✋ in the comments! 🇪🇹✨

Photos from Addis Ababa University Cultural Center's post 14/05/2026

55ኛው የኪነ-ጥበብ ምሽት ረቡዕ ግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ.ም በዕለቱም ታዋቂው ድምፃዊ ዳዊት ጽጌ የክብር እንግዳችን ሆኖ በመካከላችን በመገኘት ሙያዊ ልምዱን ያካፍለናል።

እንዲሁም ግጥሞች ፣ ወግ ፣ ሙዚቃና ሞኖሎግ ተሰናድቶ እናንተን ውድ ታዳሚዎቻችንን በባሕል ማዕከል አዳራሽ ከቀኑ 11:30 ጀምሮ ይጠብቃችኋል።

ማስታወሻ ፦ ፕሮግራሙ ላይ ለመታደም የምትፈልጉ በአሁን ሰዓት የዩኒቨርሲቲው ተማሪ ያልሆናችሁ የስነ-ጽሑፍ አፍቃሪያን በሙሉ መግቢያው በ5ተኛ በር በኩል ነው።

🎭 ያመለጡዎት ትዝታዎች አሉ? ወይስ አዳዲስ ዝግጅቶችን እየጠበቁ ነው? 🎭
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል (AAU CC) በቅርቡ ያከናወናቸውን ድንቅ የዝግጅት ትውስታዎች (Event Recaps)፣ አንጸባራቂ ፎቶዎች እና የሚመጡ ታላላቅ ፕሮግራሞችን በማህበራዊ ገጾቻችን እያጋራን ነው!
አሁኑኑ ይቀላቀሉን - አንድም ዝግጅት እንዳያመልጥዎት!
✨ በቲክቶክ - የዝግጅቶቻችንን አጫጭር እና ደማቅ ቪዲዮዎች
(Recaps) ለማየት: 👉

www.tiktok.com/
📸 በኢንስታግራም - ውብ የሆኑ የፎቶ ስብስቦችን ለመመልከት:
👉https://www.instagram.com/aau__cc?igsh=MWxzb2h6N2R1aXFpaQ%3D%3D&utm_source=qr

📰 በፌስቡክ - ያለፉ ዝግጅቶች ግምገማ እና የወደፊት ፕሮግራሞችን ለማወቅ:
👉https://www.facebook.com/share/1AqFqGNvMt/?mibextid=wwXIfr

Page
🚀 በቴሌግራም - ፈጣን የቪዲዮ እና የፎቶ ማሳወቂያዎች እንዲደርሶት: 👉
https://t.me/aau_cc

14/05/2026

ታሪካዊው 55ኛው የአንጋፋ የኪነ-ጥበብ ምሽት ከዳዊት ጽጌ ጋር! 🌟 What an unforgettable night of art and culture at AAU. 🎨💥

14/05/2026

Outdoor stages, beautiful music, poetry, and unforgettable memories. 🎭 Week 55 of Angafa Art Night was a masterpiece. Thank you to everyone who made it happen! 🥂✨

Photos from Addis Ababa University Cultural Center's post 13/05/2026

እኛ እየተዘጋጀ ነው እናንተስ
55ኛ ሳምንት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፊልም እና ቴአትር ጥበባት ትምህርት ቤት አንጋፋ የኪነ ጥበብ በምሽት የአንድ ወግ የአንድ ግጥም እንግዳችንን
ድምፃዊ ዳዊት ጽጌ ለመቀበል ዝግጅት እየጨረስን ነው ።

ቦታ ወናው ግቢ ባህል ማዕከል ፊት። 🥁እኛ ተዘጋጅተናል እናንተስ 🎸. 11:30 እንገናኝ

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address

Addis Ababa University
Addis Ababa
1000