ATLAS BUSINESS AND TECHNOLOGY COLLEGE ethiopia

ATLAS BUSINESS AND TECHNOLOGY COLLEGE ethiopia

Share

"Your Education, Your Way" Atlas Business and Technology College has a wealth of resources and wonderful people who make our community a distinctive place.

The fresh thinking, innovative spirit, and dedicated service ethic that thrive at Atlas Business and Technology College. ABTC is one that truly values the individual and the pursuit of knowledge. These are only a few reasons I chose Atlas Business and Technology College
Atlas Business and Technology College offers an exceptional learning environment in which students gain the knowledge and skills

11/06/2026

የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ወቅታዊ መረጃ

ለፈተና ተቀማጭ ተማሪዎች የተሰጡ መመሪያዎችና ደንቦች

የፈተና ተፈታኞች ኃላፊነቶች

ፈተናው ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃ በፊት የማንነት መታወቂያዎን (ID) በመያዝ በፈተና ክፍሉ ውስጥ ይገኙ።

ፈተናው ከተጀመረ ከ15 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው!

ፈተናው በጀመረ በመጀመሪያዎቹ 30 ደቂቃዎች ውስጥ ከፈተና ክፍል መውጣት አይፈቀድም።

በተሰጠዎት ነጭ ወረቀት ላይ የተጠቃሚ ስምዎን (Username) እና የይለፍ ቃልዎን (Password) ጽፈው በጥንቃቄ ይያዙ።

በፈተና ተቆጣጣሪዎች በተመደበልዎት ወንበር ላይ ብቻ ይቀመጡ።

የእርስዎን ኮምፒውተር ብቻ ይጠቀሙ እና ይክፈቱ።

በፈተና ክፍል ውስጥ ማውራትም ሆነ መዘዋወር በጥብቅ የተከለከለ ነው።

በአጠገብዎ ያለውን ተማሪ ኮምፒውተር ለማየት አይሞክሩ።

በፈተና ክፍሉ ውስጥ የሞባይል ስልክዎን ያጥፉ።

ማንኛውንም ዓይነት ወረቀት ወደ ፈተና ክፍል ይዞ መግባት አይቻልም።

ከማንኛውም ዓይነት የማጭበርበር ወይም የኩረጃ ተግባር ይቆጠቡ።

የፈተና ተቆጣጣሪዎችን እና አስተባባሪዎችን መመሪያዎች በትክክል ይከተሉ።

መልካም ዕድል! 🙏



Instructions and Guidelines for the Exit Exam

Responsibilities of Students Taking this Exam

1. Arrive at the exam room 30 minutes early with your ID.

2. Do not stop studying more than 15 minutes after the exam has started!

3. Do not leave the exam room within the first 30 minutes after the exam has started.

4. Write down and keep your Username and Password on the white paper provided.

5. Only sit in the seat assigned by the exam supervisors.

6. Use and open only your own computer.

7. Do not talk or move around the exam room.

8. Do not look at the computer of the student next to you.

9. Turn off your mobile phone in the exam room.

10. Do not bring any papers into the exam room.

11. Avoid and do not participate in any form of cheating or fraud.

12. Follow the instructions of the exam supervisors and coordinators.

Good luck 🙏

06/06/2026

ከ560 ሺህ በላይ ተፈታኞች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ለመውሰድ ተመዝግበዋል። - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍልብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 24/2018 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም ይሰጣል።

የመልቀቂያ ፈተናውን ለመውሰድ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ560 ሺህ በላይ ተፈታኞች መመዝገባቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል።

ከተመዘገቡት ውስጥ አብዛኛዎቹ ተማሪዎች ፈተናውን በበይነ-መረብ እንደሚወስዱ የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የመሰረተ ልማት ውስንነት ባሉባቸው አካባቢዎች ፈተናው በወረቀት እንደሚሰጥ ገልፀዋል።

የፈተና ሒደቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ የኢንተርኔት እና የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት አስተማማኝነትን ለማረጋገጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሠራ መሆኑን ኃላፊው ጠቁመዋል።

Telegram: Join Group Chat

05/06/2026



ትምህርት ሚኒስቴር “ኤጀንቲክ መምህር ረዳት” የተሰኘ የሰው ሰራሽ አስተውሎት መተግበሪያ አበልፅጎ በሙከራ ደረጃ ሥራ ላይ አውሏል።

Agentic AI Teacher Assistant የተባለው መተግበሪያው፣ ሙሉ በሙሉ ያለ ኢንተርኔት የሚሠራ፣ ራሱን ችሎ ውሳኔዎችን ማመንጨት የሚችል እና የሁለተኛ ደረጃ መምህራንን የሥራ ጫና የሚቀንስ መሆኑ ተገልጿል፡፡

መተግበሪያው በውስጥ አቅም የበለፀገና በአካባቢያዊ ኮምፒውተር (Local Machine) ላይ በቀላሉ ተጭኖ የሚሠራ መሆኑን በሚኒስቴሩ ‎የአይሲቲና ዲጂታል ትምህርት መሪ ስራ አስፈጻሚ ዘላለም አሰፋ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

‎መተግበሪያው በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ያሉትን መፅሐፍቶች በሙሉ ዳታሴት አድርጎ በመውሰድ፣ መፃሕፍቱን ሙሉ በሙሉ እንዲመረምርና እንዲገነዘብ ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል።

‎መተግበሪያው ምን ምን ይሠራል?

➫ የትምህርት እቅድ (Lesson Plan) ያዘጋጃል፣
➫ የፈተና ጥያቄዎችና አሳይመንቶችን ያመነጫል፣
➫ ማስተማሪያ ስልቶችን (Pedagogical Strategies) በራሱ ማቀናጀት ይችላል።

መተግበሪያው በማንኛውም ላፕቶፕ ወይም ዴስክቶፕ ላይ ተጭኖ የሚሠራ ሲሆን፤ ‎በተመረጡ ትምህርት ቤቶች ተሞክሮ አጥጋቢ ውጤት ማስገኘቱ ተመላክቷል፡፡

መተግበሪያውን ለመጠቀም ምንም አይነት ወርሃዊ የኢንተርኔት ካርድ፣ የኔትዎርክ ዝርጋታ ወይም የኤአይ አጠቃቀም ክፍያ እንደማይጠይቅ በሚኒስቴሩ ‎የአይሲቲ አማካሪ ሙሉነህ አጥናፉ (ዶ/ር) አስረድተዋል።

ከሁሉም ክልሎች ለተውጣጡ መምህራን እና የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች በመተግበሪያው አጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና መሰጠቱ ተገልጿል።

Telegram: Join Group Chat

05/06/2026

የexit exam ተፈታኞች በአስቸኳይ የማረጋገጥ ወይም self verification እንድታደርጉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።
ይህንን መረጃ ለጓደኞቻችሁ እና ለexit exam ተፈታኞች ጭምር ሼር አድርጉላቸው።

የማረጋገጥ ሥራው (Self Verification) ከ2-3 ደቂቃዎች ብቻ የሚወስድና የተፈታኞችን የትምህርት ሰነዶች ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ለማስተሳሰር እና መረጃዎቹ ትክክለኛ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው።

https://verify.ethernet.edu.et

ከላይ ባለው ሊንክ በመግባት ማረጋገጥ ትችላላችሁ።

exit exam ከ ሰኔ 4 ጀምሮ እንደሚሰጥ ይታወቃል።ስለዚህ በዛ መሰረት ዝግጅታችሁን እያደረጋችሁ መቆየት ይኖርባችኋል።

Photos from ATLAS BUSINESS AND TECHNOLOGY COLLEGE ethiopia's post 05/06/2026

ማስታወቂያ
****
መውጫ ፈተና (EXIT EXAM) ለመፈተን ለተዘጋጃችሁ የኮሌጃችን ተማሪዎች በሙሉ

የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ለመውጫ ፈተና የተፈታኞች መረጃ upload ለማድረግ የከፍተኛ ትምህርት በመውጫ ፈተና software template እንድንመዘግብ ዛሬ ግንቦት 27/2018ዓ/ም Educational Assessment and Examinations Service-EAES እና Ministry of Education Ethiopia አሳውቋል።

በመሆኑም upload ተጠናቆ ማንነታችሁን በፋይዳ አማካይነት verify የሚታደርጉበት link እስኪለቀቅ በትዕግሥት እንድትጠባበቁ እየገለጽን ለመውጫ ፈተናው ዝግጅታችሁን እንድታጠናክሩ እናሳስባለን።

25/05/2026
23/05/2026

የትምህርት ምዘናና ምርምር ለትምህርት ጥራት መሻሻልና ለትምህርት ልማት ዕድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ በላቀ ደረጃ እንዲያበረክት እየሠራ መሆኑን አገልግሎቱ ያስታወቀ ሲሆን ባለድርሻ አካላትንም አመስግኗል።

በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከሚያዚያ 26 - ግንቦት 07/2018 ዓ.ም በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ላይ በ359 ትምህርት ቤቶች ስካሄድ የነበረዉ የመሠረታዊ የንባብና የስሌት (EGRA እና EGMA) ጥናትና ምርምር መረጃ በተሳካ ሁኔታ ተሰብስቦ ተጠናቋል።

ስለሆነም መረጃው በጥራት እና በታቀደው የጊዜ ገደብ ተሰብስቦ እንዲጠናቀቅ የጎላ አስተዋጽኦ ያበረከቱትን ክቡራን የትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችን፣ የዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊዎችንና ባለሙያዎችን፣ የወረዳ የትምህርት ጽ/ቤት አመራርና ባለሙያዎችን እንዲሁም የትምህርት ቤት ርዕሰ-መምህራንንና መምህራንን ከልብ እናመሰግናለን።

የጥናት ውጤቱ መረጃው ተተንትኖ፣ ሪፖርት ተዘጋጅቶ፣ ግኝቶቹና ምክረ ሐሳቦቹም ተለይተው ሲቀርቡ በባለድርሻ አካላት ከተተቸ በኃላ ለሁሉም ባለድርሻ አካላት በይፋ የሚቀርብ ይሆናል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
ግንቦት 2018 ዓ/

21/05/2026




የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 24 ቀን እስከ ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ይሰጣል።

በዘንድሮው ሀገር ፈተና 564,219 ተማሪዎች ለፈተና ይቀመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

✅ የተፈጥሮ ሳይንስ ፦ 306,964 ተማሪዎች፤

✅ የማህበራዊ ሳይንስ ፦ 257,255 ተማሪዎች

ለፈተናው 667 ማዕከላት እንደተዘጋጁ ተገልጿል።

ፈተናው በዋናነት በበይነ መረብ (Online) የሚሰጥ ሲሆን በተለያዩ አስገዳጅና ልዩ ምክንያቶች ቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ ተማሪዎች ብቻ በወረቀት ይፈተናሉ።

17/05/2026

በድጋሚ የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የሚጠባበቁ ተማሪዎች እስከ ግንቦት 12 ድረስ ምዝገባቸውን እንዲያካሂዱ ጥሪ ቀርቧል።

የቅድመ-ምረቃ ትምህርት የመውጫ ፈተና በድጋሚ በግል ለመፈተን እየጠበቁ የሚገኙ አመልካቾች ምዝገባ ከዛሬ ግንቦት 08 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ5 ተከታታይ ቀናት ይካሔዳል፡፡

የመመዝገቢያ ሊንኩን https://exam.ethernet.edu.et በመጠቀምና የተዘረዘሩ መስፈርቶችን በማሟላት እስከ ግንቦት 12/2018 ዓ.ም መመዝገብ የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ተፈታኞች የአገልግሎት ክፍያ 750 ብር በቴሌብር በኩል መክፈል የሚጠበቅባቸው ሲሆን ፤ ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ የግድ የሚያስፈልግ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የ2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ከሰኔ 02-12/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወሳል፡፡

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Addis Ababa
2142