Menelik II Medical and Health Science College

Menelik II Medical and Health Science College

Share

Established in 1949 as Auxiliary Health Science Training School, Menelik II Health Science College is the first Nursing School in the history of the country.

Beginning from its foundation, the School has offered unreserved trainings to significant number of health assistants.In 1997 it has launched a strategy to open new training programs by delivering different courses in Junior Clinical Nursing, Public Health, Midwifery, Medical Laboratory Technology, Pharmacy and Radiography in certificate level. In 2008 the School has upgraded itself into Menelik I

13/06/2026

የሀዘን መግለጫ!

የዳግማዊ ምኒልክ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሁለተኛ ዲግሪ (MPH in Epidemiology ) የሶስተኛ ዓመት ተመራቂ ተማሪ የነበረው ዶ/ር ኤልያስ ታምራት በድንገተኛና ያልተጠበቀ ህልፈተ ሕይወት የተሰማውን ከፍተኛ ሐዘን ይገልጻል። በኮሌጃችን ተማሪ ድነገተኛ ህልፈት መሪር ሀዘን ለደረሰባቸው ለባለቤታቸው፣ ለጓደኞቻቸው እና በሕይወት ዘመናቸው በበጎ ለቀረቧቸው ሁሉ ልባዊ መፅናናትን እንመኛለን።
የአስከሬን ሽኝት የሚካሄደው ዛሬ ማለትም 6-10-2018 ዓ/ም ከቀኑ 7፡30 ቤተል ዓለም ብርሀን መሰረተ ክርስቶስ ቤተ-ከርስቲያን ሲሆን የቀብር ሥነ-ሥርዓቱ የሚፈፀመው ደግሞ በቤተል አንፎ ሥላሴ ቤተክርስቲያን ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ ይሆናል።

የዳግማዊ ሚኒልክ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

Photos from Menelik II Medical and Health Science College's post 09/06/2026

Menelik II Medical and Health Science College has conducted the 2018 E.C. Mock Examination for graduating students across all departments.

The examination was organized to assess students' readiness for the upcoming National Exit Examination, identify areas requiring improvement, and provide valuable experience with the examination environment.

The mock examination provided students with an opportunity to familiarize themselves with the format, standards, and time management requirements of the national assessment. It also enabled the College to evaluate the effectiveness of its academic preparation efforts and identify areas where additional support may be required. The results of the mock examination will serve as an important input for targeted interventions aimed at enhancing student performance and success in the National Exit Examination.

Photos from Menelik II Medical and Health Science College's post 05/06/2026

Congratulations to the Class of 2026 on successfully defending your research projects!

This remarkable achievement marks a significant milestone in your academic journey and reflects your dedication to advancing health science through research and innovation. Your hard work, perseverance, and commitment to excellence have prepared you to make meaningful contributions to improving health outcomes and addressing tomorrow's challenges.
The future is yours to shape!

]

Photos from Menelik II Medical and Health Science College's post 04/06/2026

የ2018 ዓ/ም የሁለተኛ ዙር የቡድን ስልጠና /TTP/ ማጠቃለያ ፕሮገራም በዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳንስ ኮሌጅ ተካሄደ፡፡


መርሃ ግብሩን በንግግር የከፈቱት የኮሌጁ ችፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬከተር አማካሪ አቶ ጥበቡ ቸርነት እጩ ተመራቂ ተማሪዎቹ በስድስት ሳምንታት የመስክ ቆይታቸው ያሳዩት የላቀ አፈፃፀምና በማህበረሰቡ እንዲሁም በተለያዩ የህዝብ ተቋማት ውስጥ ያመጡት ተጨባጭ ለውጥ ከፍተኛ መሆኑን በመግለጽ ኮሌጁ በንድፈ-ሀሳብ የሚያስተምረውራቸውን ትምህርቶች በተግባር ለመደገፍ ችግሮችን በመለየትና መፍትሄዎችን በመሻት እጩ ተመራቂ ተማሪዎቹ ያሳዩት ተግባር በግልፅ ያየንበት መድረክ ነው ብለዋል።አክለውም፣ ለዚህ ትልቅ ስኬት መገኘት ሌሊትና ቀን ለደከሙት ተማሪዎች፣ ሙያዊ ክትትልና የአካዳሚክ ድጋፍ ላደረጉ የኮሌጁ መምህራንና ሰራተኞች እንዲሁም ስራው ውጤታማ እንዲሆን አጋርነታቸውን ላሳዩ አካላት ፣ የተለያዩ ክፍለ ከተማ እና የጤናው ዘርፍ ባለድርሻ አካላት በሙሉ በኮሌጁ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በየኮሌጁ ችፍ ምርምር፣ ክሊኒካል እና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር ዶ/ር ፍቅርተ ወ/ሰላሴ የቡድን ስላጠና ፐሮገራሙ (Team Training Program) በማህበረሰቡ ውስጥ ሳይንሳዊ የዳሰሳ ጥናት በማደረግ ፣ የአካባቢውን አንገብጋቢ የጤና ችግሮች በመለየትና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ደረጃ በማስያዝ ተጨባጭና የሆኑ ስራዎችን በመሰራት ላደረጉት ሙያዊ አበረክቶ እጩ ተመራቂ ተማሪዎችን አመስግነዋል፡፡

ሁሉም የቀረቡት ፕሮጀክቶች የቡድን ስራ እና የችግር ፈቺነት ብቃትን ያጎሉ ሲሆን፤ በቡድኖቹ ለቀረቡት ስረዎች ፣ ስለተጠቀሙባቸው ስልቶች እና ባቀረቧቸው መፍትሄዎች ላይ ስለሚኖረው ውጤት ውይይት ተደርጓል፡፡ ፕሮግራሙ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጤና አገልግሎት እድገት አስተዋጽኦ ማበርከት የሚችል ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት እያደረገ ያለውን ቀጣይነት ያለው ጥረት ከመደገፉም በላይ ሁሉን አቀፍ የጤና መሻሻል ጥረቶችን በማሳየትና መፍትሄዎችን በማመላከት ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡

በመጨረሻም የእለቱን መርሃ ግብር በንግግር የዘጉት የኮሌጁ ችፍ አካዳሚክ ዳይሬከተር ዶ/ር ደረጀ ደርበው በእጩ ተመራቂ ተማሪዎች የተሰሩት ፕሮጀክቶች ከተማ አስተዳደሩ ለጀመረውና እያከናወነ ላለው ሁሉን አቀፍ የጤና መሻሻያ ስራዎች የሚኖራቸውን አስተዋፅኦ በመግለፅ ኮሌጁ የህክምና እውቀትን ከተግባራዊ የህዝብ አገልግሎት ጋር በማስተሳሰር የአካባቢውን ማህበረሰብና የመንግስት ተቋማትን ተጠቃሚነት የማሚደግፉ ብቁ የጤና ባለሙያዎችን የማፍራት አገራዊ ተልዕኮውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል እብራርተዋል፡፡ ለወደፊትም የቡድን ስላጠና ፐሮገራሙ (Team Training Program) የበለጠ በማጠናከር ከአዲስ አበባ ከተማ አዋሳኝ የማሀበረሰብ ክፊሎች ላይም እንደሚሰራ አመላክተዋል፡፡

Photos from Menelik II Medical and Health Science College's post 04/06/2026

በዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የዲጅታል ላይበራሪ ሲስተም በኮሌጁ ኮምፒውተር ሳይንስ ባለሙያዎች ተሠርቶ የዳታ ማስገባት ዛሬ ማለትም 27-09-2018 ዓ/ም ሥራ ጀመሯል፡፡

እንደሚታወቀው በአሁኑ ጊዜ በሀገራችን በተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የዲጅታል ለውጥ ከመቸውም ጊዜ በላይ እየተፋጠነ ይገኛል፡፡ ኮሌጁም እንደ አንድ ከፍተኛ የጤና ትምህርት ተቋም የዚህን የድጅታል ለውጥ ለማሳካት ባደረገው ጥረት በኮሌጁ የዲጅታል ላይበራሪ ሲስተም በራሱ በኮሌጁ ባለሙያዎች ተሰርቶ የዳታ ማስገባት ሥራ በዛሬው ቀን በይፋ ተጀምሯል።

ይህንንም ስራ በይፋ ለማስጀመር የኮሌጁ ማኔጅመንት አባላት የተገኙ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ በተቋሙ ውስጥ ባለ የሰው ኃይል እና በአነስተኛ ወጪ መገንባቱ እንደ መልካም ልምድ ሊወሰድ ይችላል ብለዋል፡፡

የድጅታል ቤተ-መጽሃፈት ሲስተሙን በይፋ መጀመሩን ያበሰሩት የኮሌጁ ችፍ ኤክስኪቲቭ ዳይሬከተር አቶ አለሙ ዳንኤል በመክፈቻው ንግግራቸው እንደገለፁት፣ ሲስተሙ በውስጥ አቅም መገንባቱ ተቋሙ በዲጅታል ለውጥ መንገድ ላይ ያሳየው ጠንካራ እርምጃ መሆኑን ገልፀው ቀሪ ስራዎችም በተመሳሳይ መነሳሳት እንዲጠናቀቁ አሳስበዋል።

በአጠቃላይ፣ ይህ ፕሮጀክት ተቋሙን ወደ ዘመናዊ ዲጅታል በተ-መጽኀፍት አስተዳደር ለመውሰድ እንደ አንድ ጠንካራ እርምጃ የሚወሰድ ሲሆን፣ በሀገሪቱ ባሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እየተካሄደ ያለውን የዲጅታል ለውጥ አንዱ አካል መሆኑ ይታመናል።

Photos from Menelik II Medical and Health Science College's post 30/05/2026

Mock Examination Successfully Conducted at Menelik II Medical and Health Science College


Menelik II Medical and Health Science College has conducted a two-round mock examination for students across all departments. A total of 368 graduating students participated in the assessment.


We organized the mock examination to prepare students for the upcoming national exit examination and give them practical experience with Computer-Based Testing (CBT). The exercise enabled students to familiarize themselves with the examination environment, improve their test-taking skills, and build confidence ahead of the national assessment.


By familiarizing students with digital formatting and navigation, the college simulated the official exam environment, reducing technical anxiety and building test-taking stamina. Experiencing these realistic conditions firsthand means our students are now significantly better prepared to conquer their final hurdles. Finally, the college extends its heartfelt thanks to our school deans, directors, and technical coordination teams who worked tirelessly to ensure both rounds ran seamlessly.


Photos from Menelik II Medical and Health Science College's post 29/05/2026

የ2018 ዓ/ም የሁለተኛ ዙር የቡድን ስልጠና /TTP/ ከሁሉም ት/ት ክፈሎች በተሰማሩ እጩ ተመራቂ ተማሪዎች ከአንድ ወር ከ 15 ቀናት ቆይታ በኋላ ዛሬ ማለትም 21-09-2018 ዓ/ም ተጠናቀቀ፡፡

በዚሁ መሰረት ከሚያዚያ 12-08-208 ዓ/ም እስከ ግንቦት 21-09-2018 ዓ/ም ሲከናወን የቆየው የዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የ2018 ዓ/ም የዚህ ዙር የቡድን ስልጠና /TTP/ 277 እጩ ተመራቂ ተማሪዎች ከሰባት ክፍለ ከተሞች በተመረጡ 07 ወረዳዎችና ከወረዳው በተመረጡ የማህበረሰብ ክፍሎች ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የተለዩ የማህበረስብ ችግሮችን መሰረት በማድረግ ፕሮጀክት በመቅረጽ በየአካባቢው ከሚገኙ የመንግስት አካላት፤ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች እንዲሁም መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመሆን ለማህበረሰቡ የተሰሩ ፐሮጀክቶችን ተጠናቀዋል፡፡

የፕሮጀክቶቹን መጠናቀቅ ምክንያት በማደረግ የኮለጁ የማኔጅመንት አባላት በተለያዩ ሳይቶች በመገኘት ከማሀበረሰቡ ጋር ቀጣይ በኮሌጁ በማህበረሰቡ ውስጥ ለሚሰሩ ስራዎች ተወያይተዋል፡፡ በዚሀም መሰረት የኮሌጁ ችፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬከተር አቶ አለሙ ዳንኤል በ.አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ ለገላን ጤና ጣቢያ እና በፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የኮሉጁ ችፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬከተር አማካሪ አቶ ጥበቡ ቸርነት ቃሊቲ ክ/ከ በገላን ጤና ጣቢያ እና በፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን እና በአራዳ ክ/ከ ራስእምሩ ጤና ጣቢያና አካባቢው ፣ የኮሌጁ ችፍ ምርምር፣ ክሊኒካል እና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር ዶ/ር ፍቅርተ ወ/ሰላሴ በየካ ክ/ከተማ ጨፌ ወረዳ 08 ጤና ጣቢያና አካባቢው፣ የኮሌጁ ችፍ አካዳሚክ ዳይሬክተር ዶ/ር ደረጀ ደርበው በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከ ወረዳ 09 ጤና ጣቢያና አካባቢው፣ የኮሌጁ ችፍ አስተዳደርና ልማት ዳይሬክተር አቶ ዱሬሳ ሙላቱ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ወረዳ 10 ጤና ጣቢያና አካባቢው እንዲሁም አቶ በላቸው አእምሮ የኮሌጁ ቲቲፒ ፣ ሲቢቲፒ እና ኦስኪ ዳይሬክተር በአዲስ ከተማ ክ/ከ ሚሊኒየም ጤና ጣቢያና አካባቢው ላይ የተሰሩ ስራዎችን ለማህበረሰቡ አስረክበዋል፡፡

እነዚህ ጤና ነክ ፕሮጀክቶች ከተማ አስተዳደሩ ለጀመረውና እያከናወነ ላለው ሁሉን አቀፍ የጤና መሻሻል ጥረቶችን በማገዝ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከማበርከታቸውም በላይ ማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ ችገሮችን የማህበረሰብን ንቅናቄ በመፍጠር መፍታት እንደሚቻል እና ወደፊትም ለሚሰሩ ስራዎች ችገሮችን ለማመላከት ወሳኝ ሚና ይኖራቸዋል፡፡

በዚህ የሁለተኛ ዙር የቡድን ስልጠና /TTP/ በተመረጡት አካባቢዎች ተማሪዎቹ በብር ሲተመን 880,000 ብር( ስምንት መቶ ሰማኒያ ሽህ ብር ) ማህበርስቡን በማሳትፍና የገንዘብና ቁሳቁስ ድጋፍ በማፈላለግ ዛሬ ማለትም 21-09-2018 ዓ/ም ፕሮጅቸቶቹ ለተሰሩባቸው ጤና ጣቢያዎች እና በተመረጡት አካባቢዎች ለተሰሩት ስራዎች ለማህበረሰቡ አስረክበዋል፡፡

27/05/2026

እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል አድሐ በዓል አደረሰን፣ አደረሳችሁ!

ስለዒድ አል-አድሐ “ዐረፋ” በዓል ስናስብ ሦስት ነገሮች ቀድመው ይታወሱናል። መስዕዋትነት፣ መታዘዝ እና መተጋገዝ። አባት ልጁን ለመስዕዋት ያቀረበበት፤ ልጅ የአባቱን ትዕዛዝ የፈጸመበት፤ ሙስሊሞች የመተጋገዝን እሴት ለዓለም የገለጡበት በዓል ስለሆነ “ዐረፋ” በሕዝበ-ሙስሊሙ ዘንድ ትልቅ ትርጉም አለው።

እስማኤል ለነብዩ ኢብራሂም የመጀመሪያ እና ተወዳጅ ልጃቸው ነው። አላህ (ሱ.ወ.) ይሄን ተወዳጅና የመጀመሪያ ልጅ እንዲሠዉለት ሲጠይቃቸው ታዘዙ እንጂ ወደኋላ አላሉም። ለመታዘዝ የሞከሩት ነገሩ ቀላል ሆኖ አይደለም። ልጅን ያህል ነገር መስዕዋት ማድረግ ምኑ ይቀላል? የአባትነት ስሜት ይተናነቃል። የሰይጣን ሹክሹክታ ይፈታተናል። የቤተዘመድን ወቀሳ እና የጎረቤትን አስተያየት መቋቋምም ይከብዳል። ነብዩ ኢብራሒም፥ በዚህ ሁሉ አጣብቂኝ ውስጥ አንድ ሐቅ ተገልጦላቸዋል። ከራስ ስሜት፣ ከሰው ሐሜት እና ከወዳጅ ፍላጎት የሚልቅ ታላቅ ዓላማ እንዳለ አምነዋል። ስለዚህም በፈተና ውስጥ ጸንተው ቆሙ፤ ቆራጥነታቸውም በተግባር ታየ።

ሀገር የምትገነባው ከራስ ጥቅም በላይ በሚያስቡ እና ከግላዊ ፍላጎታቸው በላይ ለመፈጸም በቆረጡ ዜጎች ነው። የሚወዱትን ነገር እንኳን ሳይቀር ለመሠዋት ዝግጁ የሆኑ ዜጎች ሲበዙላት ሀገር ትበረታለች። እስማኤላቸውን ለመስጠት የማያመነቱ ዜጎች የሞሉባት ሀገር ጽኑ ናት።
የለመድናቸው፣ የምንወዳቸው፣ የራሳችን ገንዘብ ያደረግናቸው ብዙ ነገሮች ይኖራሉ። ከእነዚህ የሚበልጥ ዓላማ ግን አለ፤ እሱም “ሀገርነት እና ሉአላዊነት” ይሰኛል። ሀገርነት የሚገነባው ከመውሰድ ይልቅ በመስጠት ነው። ሉአላዊነት የሚጸናው በፈተና ሳይወድቁ በመቆም፤ በወጀብ ሳይናወጡ መጓዝ በመቻል ነው።

የእውነት ኢትዮጵያ ሲያልፍላት ማየት የምንሻ ከሆነ ምኞታችን በተግባር ይገለጥ። የሀገር ኩስመና ካሳሰበን ለግዝፈቷ እንድከም። ያጎበጣትን የድህነት ቋጥኝ ለመሸከም ትከሻችንን እናመቻች። ጎተራዋ እንዲሞላ እጃችን አፈር ይንካ። የጠየመ ገጽዋ እንዲፈካ በሥራ ሌት-ተቀን እንሰለፍ። የተቀማ ክብሯ እስኪመለስ ድርሻችንን እንወጣ። ሀገር መውደዳችን ከልብ ከሆነ መስዕዋት ለመሆን አናመንታ።

የዐረፋ በዓል የመታዘዝና የመስዕዋት ብቻ ሳይሆን የመደጋገፍና የመተጋገዝ በዓል ጭምር ነው። በዐረፋ ከሚከናወነው እርድ አንድ ሦስተኛው ለምስኪኖች እንዲሰጥ የእስልምና አስተምህሮ ያዛል። በዐረፋ ሕዝበ-ሙስሊሙ ደስታና ሐዘኑን እየተጋራ በዓሉን ያከብራል። የዐረፋ እለት አንድም ሰው ተከፍቶ አያሳልፍም፤ በዐረፋ ሰሞን ማንም ሰው ተርቦና ተጠምቶ አያድርም። በዓሉ ትርጉም የሚሰጠው ሕዝበ-ሙስሊሙ ያለውን ተካፍሎ ሲያከብረው ነው። ሰዎች አስቸጋሪ ሁኔታን የሚሻገሩበት መፍትሄው መተሳሰብና መተጋገዝ እንደሆነ ከዐረፋ እንማራለን። ሀገርም ከፈተናዎችዋ በላይ እንድትሆን እኒህ እሴቶች ወሳኝ ናቸው።

ዐረፋ ማኅበረሰባዊ በዓል የሚባለው ለዚህ ነው። ሰዎች በግላቸው የሚያከብሩት አይደለም። ቤተሰቡ፣ ጎረቤቱ፣ ሠፈሩ፣ ከተማው የሚያከብረው በዓል ነው። ያላቸውና የሌላቸው፤ የሚችሉና የማይችሉ፤ ታላላቆችና ታናናሾች፤ ባለ ሥልጣናትና ተራ ዜጎች፣ በአንድነት የሚያከብሩት በዓል ነው። ሰው የሚኖረው በቤቱ ውስጥ አይደለም። በማኅበረሰቡ ውስጥ ነው።
ማኅበረሰባዊ ትሥሥርና ትብብር ለዜጎች እና ለሀገር ደኅንነት ወሳኝ ናቸው። ማኅበረሰባዊ ትሥሥር ስለሌሎች እንድናስብ፣ ስለሌሎች እንድንሠራ እና ስለ ሌሎች ዋጋ እንድንከፍል ያደርገናል። ራሳችንን በሌሎች ጫማ ላይ አቁመን እንድናይ ያስችለናል። የሁላችንም ሰላም፣ የሁላችንም ደኅንነት እና የሁላችንም ጥቅም ካልተከበረ በቀር የግላችንን ብቻ ልናስከብር እንደማንችል ያስገነዝበናል። ስለዚህም ማኅበራዊ ግዴታን እንደ ዜግነት ግዴታ ወስደን እንድንሠራ ያደርገናል።
ምርጫ ማኅበራዊና ዜግነታዊ ግዴታዎችን ከምንወጣባቸው የዴሞክራሲ መገንቢያ መሳሪያዎች መካከል ዋነኛው ነው። ያለ ሕዝብ ተሳትፎ ዴሞክራሲ አይሳካም። ያለ ምርጫም የሕዝብ ተሳትፎ ምሉዕ አይሆንም። የዴሞክራሲያችን መሰረት ጥንካሬው የሚለካው በተሳትፎአችን መጠን ነው።

የዘንድሮ ሀገራዊ ምርጫ ሀገረ-መንግሥታዊ ሥርዓታችን የሚጠነክርበት መሰረት ነው። የዴሞክራሲ ልምምዳችን አንድ ደረጃ ከፍ የሚልበት፤ የቀጣይ ዓመታት የሀገራችንን እጣ-ፈንታ የምንበይንበት፤ ከምንም በላይ ብዝሃ-ድምጽ የሚሰማበት የሕግ መወሰኛ ምክርቤት የምንመሰርትበት ወሳኝ አጋጣሚ ነው። በመሆኑም በዓሉን ስናከብር ዜግነታዊ ግዴታችንን ለመወጣት ብቻ ሳይሆን በካርዳችን ዴሞክራሲያዊ መብታችንን ለማረጋገጥ እየተዘጋጀን እንዲሆን ጥሪዬን አቀርባለሁ።

በድጋሚ መልካም የዐረፋ በዓል እንዲሆን እመኛለሁ!
ዒድ ሙባረክ!!

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!

ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ግንቦት 18፣ 2018 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Photos from Menelik II Medical and Health Science College's post 19/05/2026

የዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አጠቃላይ የክልኒካል ሰርቶ ማሳያ አጠቃቀም ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት አካሄደ።


የፓናል ውይይቱ የኮሌጁን ማንጅመንት፣ የት/ቤት ዲኖችን፣ የአካዳሚክ ዳይሬክተሮችን፣ የዲፓርትመንት ተወካዮችን፣መምህራንንና የተማሪ ተወካዮችን በማካትት የማዕከላዊ ሰኪል ላብ አጠቃቀም፣ ብሎም ያሉትን የአሰራር ልምዶች ለመገምገም፣ ክፍተቶችን ለመለየት እና የተማሪዎችን ክሊኒካዊ ብቃት እና የተግባር ልምድን ወደተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር በተግባራዊ መፍትሄዎች ላይ ተወያይቷል።

የፓነል ውይይቱን ንግግር በማደረግ የከፈቱት የኮሌጁ ችፍ ምርምር፣ክሊኒካልና ማሀበረሰብ አገልግሎት ዳይሬከተር ዶ/ር ፍቅርተ ወ/ስላሴ ሲሆኑ የኮሌጁን ማዕከላዊ ሰርቶ ማሳያ በማስፋፋትና በማዘመን ረገድ የታዩትን መልካም ስራዎች በመጠቆም ኮሌጁ አሁን ካሉት ዘመኑን የዋጁ የሰርቶ ማሳያ መሳሪያዎች አንፃር ሙሉ በሙሉ መጠቀም በትምህርጥ ጥራት ላይ የሚኖረውን ፋይዳ ጠቁመዋል፡፡በመቀጠልም የTTP(የቡድን ስልጠና ፕሮግራም)ን በተማለከተ በኮሌጁና እና በጤና ተቋማት መካከል ጠንካራ ትብብር በማድረግ የማሀበረሰቡን ችግር የሚለይና ችገሩን የሚፈታ ብቁ የጤና ባለሙያ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ጠቁመው ከሀገራዊ የትምህርት ጥራት ደረጃዎች ጋር የተጣጣመ ተግባራዊ ትምህርትን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል።

በፓነል ውይይቱ ላይ ሁለት ዋና ዋና ርዕሶች የቀረቡ ሲሆን የመጀመሪያው በኮሌጁ ማዕከላዊ ሰርቶ ማሳያ ዳይሬክተር፡ ሲስተር የወርቅዉሃ ጌታቸው “የማዕከላዊ ሰርቶ ማሳያ መልካም ተሞክሮች እና ተግዳሮቶች” በሚል ርዕስ ሁለተው ድግሞ በኮሌጁ ቲቲፒ፣ሲቢቲፒ እና ኦስኪ (TTP,CBTP AND OSCE ) ዳይሬከተር አቶ በላቸው አእምሮ የቲቲፒ(Team Training Program) ትግበራን በተመለከተ ቀርበዋል፡

የፓነሉ ተሳታዮች ማዕከላዊ ሰርቶ ማሳያ(Central Skill Lab) አጠቃቀም በሁሉም ጥምሀርት ክፍሎች ያለውን ንፅፅር የተጠቆመ ሲሆን በውጤታማነትና በትግበራ ወቅት የታዩ ክፍተቶችም ጎን ለጎን ተገምግመዋል፡ ከዚህ በተጨማሪ የተማሪዎችን በራስ መተማመን፣ ክሊኒካዊ ብቃት እና ሙያዊ ዝግጁነት ለማሳደግ የተግባር ማሳያዎችን አስፈላጊነት ላይ አስምረዋል፡፡ በዚህም ረገድ በሆስፒታሎች እና በጤና ጣቢያዎች የተማሪዎችን ክሊኒካዊ ስልጠና በተመለከተም ሰፊ ውይይቶች የተካሄዱ ሲሆን ፣ተሳታፊዎችም የቁጥጥር ስርዓትን በሚመለከት ፣ ምቹ የሆኑ የመማሪያ አካባቢዎችን ለማሻሻል ገንቢ ምክሮችንም አንስተዋል።

የኮሌጁ ችፍ አስተዳደርና ልማት ዳይሬክተር አቶ ዱሬሳ ሙላቱ ተቋሙ በሁለቱም ካምፓሶች ያሉተን የማእከላዊ ሰረቶ ማሳያ ግብዓቶች ፣የላብራቶሪ እቃዎች፣ ለፋረማሲ ሠረቶ ማሳያ የሚያያስፈልጉ መሳሪያዎችና ሪኤጀንቶችን ለማዘመን እና ለማጠናከር በአጠቃላይ ኮሌጁ ምቹና ዘመናዊ የትምህርት ግብዓችን ለማሟላት የሄደበትን ርቀት በማስተወስ ለወደፊትም ሁሉንም የሰረቶ ማሳያ ማእከሎች ዘመናዊ ለማደረግ ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል፡፡

የኮሌጁ ችፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬከተር አማካሪ አቶ ጥበቡ ቸርነት ደግሞ የተግባር ትምህርት ልምምድ ብቁና በስነ ምግባር የታነፁ የጤና ባለሙያዎችን ለማፍራት ያለውን ወሳኝ ሚና ጠቁመው የክሊኒካዊ ትምህርት ልምምድ የብሔራዊ የመውጫ ፈተናን ውጤትን ለማሻሻል ብቻ ሳይሆን ብቁ፣ በስነምግባር የታነፁ እና ህብረተሰቡን በብቃት የሚያገለግሉ የጤና ባለሙያዎችን ለማፍራት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።

የዕለቱን መርሃ ግበር የመዝጊያ ንግግር በማድረግ ያጠቃለሉት የኮሌጁ ችፍ የአካዳሚክ ዳይሬክተር ዶ/ር ደረጀ ደርበው ሲሆኑ ሁሉም ዲፓርትመንቶችና የትምህርት ቤት ዲኖች የክሊኒካል ልምምድ ማዕከላትን እና የክህሎት ላቦራቶሪዎችን ከሀገራዊ የስርአተ ትምህርት እና የጤና አጠባበቅ ትምህርት ደረጃዎች ጋር በተጣጣመ መልኩ በብቃት መጠቀም እንደሚያስፈልግ በመረዳት የትምህርትን ጥራት ልማሰጠበቅ ከመቸውም ጊዜ በላይ እንድንቀሳቀሱ በማሳሰብ ከሪክለሞቻችን ሙሉ በሙሉ በኤ.ፊ.ዲ.ሪ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን መሰርት እንድተገበሩ አሳስበዋል፡፡

Photos from Menelik II Medical and Health Science College's post 09/05/2026

የዳግማዊ ምኒልክ ሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የማህበረሰብ አገልግሎት በጌርጌሴኖን የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል በመገኘት የማሀበረሰብ አገልግሎት አከናወነ፡፡

የዳግማዊ ምኒልክ የሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከመማር ማስተማር እና ምርምር ስራዎቹ ጎን ለጎን፣ የማህበረሰብ አገልግሎት (Community Service) አንዱ ከመሆኑ አንፃር ይህን መሰረት በማድረግ፣ ዛሬ ማለትም ግንቦት 1-09-2018 ዓ/ም የኮሌጁ ሰራተኞችና ተማሪዎች በጌርጌሴኖን የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል በመገኘት ልዩ ልዩ ተግባራትን አከናውነዋል፡፡

በእለቱ በስፈራው በመገኘት ለማሀበረስብ አገልገሎትና ለሰብዓዊነት ሁሌም ኮለጁ ዝግጁ እነደሆነ ይህንንም ተግባር እነደ አንድ ማሀበራዊ ሀላፊነት እነደሚወጣ የጤና ተቋም እንደ ሁልጊዜውም አጠናክሮ እንደሚቀጥል የኮሌጁ ማኔጅመት አባለት ማለትም( ደ/ር ደረጀ ደርበው፣ ችፍ አካዳሚክ ዳይሬከተር፡ ዶ/ር ፍቅርተ ወ/ስላሴ፣ ችፍ ምርምር፡ ክሊኒካልና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬከተር፣ አቶ ዱሬሳ ሙላቱ፣ ችፍ አስተዳደርና ልማት ዳይሬከተር እና አቶ ጥበቡ ቸርነት፣ የችፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬከተር አማካሪ) በስነ-ሰርዓቱ ላይ በመገኘት ባደረጉት ንግግር አረጋግጠዋል፡፡

በጠቃላይ በእለቱ ለማዕከሉ ከተደረገው ድጋፍ መካከልም፡
1. የሕክምና እና የጤና እንክብካቤ አገልግሎት፡ በነዚህ ተገባራት የተለያዩ የጤና ባለሙያዎችና ተማሪዎች በማስተባበር ለማዕከሉ የአእምሮ ህሙማን በየደረጃው የተለያዩ የሕክምና ድጋፍ ተሰጥቷል። ከዚህም በተጨማሪ የኮሌጁ ማሀበረሰብ በህሙማኖቹ መካከል በመገኘት በስነ-አእምሮ ጤና ባለሙያዎች አዕምሮ የህክምና ድጋፍ፡ ፡ የደም ግፊት ልየታ እና የግል ንፅህናቸው ጥበቅና እንክብካቤ ተግባራት ተከናውነዋል። ።
2. የቁሳቁስ ድጋፍ፡ ለማዕከሉ ተረጂዎች የዕለት ተዕለት ፍጆታ የሚውሉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ያበረከተ ሲሆን፣ በዚህም መሰረት አጠቃላይ ዋጋ 112,028.80 (አንድ መቶ አስራ ሰባት ሺህ ሃያ ስምንት ብር ከሰማንያ ሳንቲም) የሚተመን ቁሳቁስ
3. በገንዘብ ፡15, 000( አስራ አምስት ሽህ ብር)
በአጠቃላይ 117,028.80 (አንድ መቶ አስራ ሰባት ሺህ ሃያ ስምንት ብር ከሰማንያ ሳንቲም) የሚተመን ድጋፍ አድርጓል፡፡

በአጠቃላይ ይህ ተግባር ኮሌጁ ለማህበረሰብ አገልግሎት የሚሰጠውን ትኩረት የሚያሳይ ሲሆን ወደፊትም መሰል የበጎ አድራጎት ስራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል የዜጎችን ጤናና ደህንነት ለመጠበቅ ያለውን ቁርጠኝነት በመግለፅ በተለያየ ምክንያት ድጋፍ ለሚያስፈልጋችው ሰዎች ድጋፍን በመለገስ ማሀበረሰባዊ ሃላፊነቱን ይወጣል።

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Address


Menelik II Medical And Health Science College Interstate Located Near Kebena Square( Specifically Inside Menelik II Referral Hospital) Latitude: 9. 0389185 Longitude: 38. 7750979
Addis Ababa
3268