Rebuni ረቡኒ

Rebuni ረቡኒ

Share

doctrinal, and theological teachings of the Ethiopian Orthodox Church.

ረቡኒ ቃሉ የእብራይስጥ ሲሆን ትርጉሙም መምህር ማለት፡፡ በዚህም ፔጅ ላይ ምእመኑን ሊያስተምሩ የሚችሉ ሀይሞኖታዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮችን ያነሳል … ከምእመናን የሚነሱለትን ጥያቄዎች የቤተ-ክርስቲያን መምህራንን በማናገር መጻህፍትን በማገላበጥ ምላሽ ይሰጣል … እባካችሁ ቤተ-ክርስቲያን ምላሽ የማትሰጥበት ጥያቄ የለምና ተገቢውን አካል እንጠይቅ እንማማር ለበለጠ መገጃ www.rebuni.com በመጎብኘት ይሳተፉ፡፡ ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን የእመቤታችን የቅዱሳን ምልጃ አይለየን፡፡

05/06/2026
Photos from Rebuni ረቡኒ's post 03/06/2026

#በልቡናችን ውስጥ "እስከ መቼ?" የሚል የቁጭትና የኀዘን ጥያቄን ፈጥሯል!!
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ

#የአገልጋዮችህን በድኖች ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ፣ #የቅዱሳንህንም ሥጋ ለምድር አራዊት።”
መዝሙረ ዳዊት 78÷2

#በአርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ፣ በሽርካ፣ በሆንቆሎ፣ በዋቤና በሙኔሳ ወረዳዎች በመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችንና በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ ስለደረሰው #አሰቃቂ ጥቃት የሰማነው በተሰበረ ልብ ነው።

#የእምነት ነፃነት ተደፍሮ 100 ዓመታት ያስቆጠረው የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን #በመቃጠሉ፣ የካራ ኩፍቴና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን #ተዘርፎ በርካታ ምእመናን በግፍ #በመሰዋታቸው፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ከቀዬአቸው #በመፈናቀላቸው በእጅጉ አዝነናል።

#ምእመናን የምታጽናናውና የሰላም፣ #የፍቅርና የታሪክ ማህደር የሆነችው ቤተ ክርስቲያን በዚህ ወቅት ፈተና ውስጥ ከመሆኗም በላይ #በአርሲ ምድር በተደጋጋሚ የሚስተዋለው #በደልና ግፍ በሁላችንም ልቡና ውስጥ "እስከ መቼ?" የሚል #የቁጭትና የኀዘን ጥያቄን ፈጥሯል።

#መከራው እየሰፋ በመምጣቱ #የጸጥታ አካላትና በየመዋቅሩ ያላችሁ ሓላፊዎች በሥልጣን ዘመናችሁ የዜጎች ደኅንነት በመጠበቅ፣ የጥቃት ሰንሰለቱን በማስቆምና ወንጀለኞችን ለሕግ በማቅረብ #ከታሪክ ባለዕዳነት ትድኑ ዘንድ በቤተ ክርስቲያናችን ስም አበክረን እናሳስባለን።

#በየአካባቢው የምትገኙ #ምእመናንና መላው ኢትዮጵያውያንም በወንድማማችነት መንፈስ #ተጋግዛችሁ፣ የተፈናቀሉ ወገኖችን በመደገፍና በጸሎት ከቤተክርስቲያናችን ጎን እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

#ቤተ ክርስቲያናችን ሁል ጊዜ ለሰላም፣ ለይቅርታና ለሰው ልጆች ክብር የምትቆም ሲሆን አምላካችን ይህንን የኀዘን ሰዓት #በምሕረቱ ያሳልፍልን፣ የሞቱትን ነፍስ በመንግሥቱ ይቀበልልን፣ የተጎዱትንም በቸርነቱ ያጽናናልን፡፡

#እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!

Photos from Rebuni ረቡኒ's post 02/06/2026

#ስለ አንተ ቀኑን ሙሉ እንገደላለን እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ጌታ ሆይ አንተን የሚያውቅ ይሰደዳል!
ሮሜ 8:36

#በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ከ10 በላይ ኦርቶዶክሳውያን ሲገደሉ የ101 ዓመት እድሜ ያለው የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት ወድሟል።

#የመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ላይም ዘረፋ የተካሄደ ሲሆን ምእመናን ጽላቱን ይዘው ተሰደዋል፤ መኖሪያ ቤታቸውም ተቃጥሏል።

#እንደ ወትሮው ሁሉ ዛሬም በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ማቅ የለበሱ እናቶች፣ እንባቸው ያላለቀ ሕፃናትና ማደሪያ ያጡ አረጋውያን ጩኸት ሰሚ አጥቷል።

#ከግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት፣ አሰኮ ወረዳ፣ ጠላታ ጨፋ ቀበሌና ካራ ኩፍቴና በሚባሉ አካባቢዎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ ያነጣጠረ አሰቃቂ ግድያ ተፈጽሟል።
#እጅግ አሳዛኝና አረመኔያዊ በነበረው ጭፍጨፋ በአሰኮ ወረዳ ጠላታ ጨፋ ቀበሌ ብቻ በታጣቂ ኃይሎች በተፈጸመ ጥቃት ከ10 በላይ ንጹሃን ኦርቶዶክሳውያን ተገድለዋል።

#የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም የሚፈተትበት መቅደስ ላይ ኢላማ ባደረገ ጥቃትም በአካባቢው የሚገኘውና 101 ዓመታት ያስቆጠረው፣ የዕድሜ ባለጸጋው የጠላታ ጨፋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት ወድሟል።

#በተመሳሳይ ጥቃት በካራ ኩፍቴና መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ላይ ጥቃት የተሰነዘረ ሲሆን፣ የቤተክርስቲያኑ ንብረት የሆኑ ቤቶች በመቃጠላቸው ምእመናን የመድኃኔዓለምን ቅዱስ ጽላት ይዘው በእግራቸው ወደሌላ አካባቢ መሸሻቸው ታውቋል።

#ኦርቶዶክሳውያኑ ተወልደው ካደጉበት፣ ወልደው ከሳሙበት ቀያቸው በሃይማኖታቸው ብቻ ቤታቸው እየተለየ ተቃጥሏል፤ ንብረታቸውና ከብቶቻቸው ተዘርፈዋል።

#ከጥቃቱ የተረፉት ነዋሪዎችም ይዘውት የሸሹት እምነታቸውንና ማንነታቸውን ብቻ በመሆኑ አሁን ላይ ሜዳ ላይ ወድቀው ይገኛሉ ሲሉ ነበር በሃዘን ተውጠው የነገሩን።

#በተያያዘ ዜና በዚሁ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በሺርካ ወረዳ በሁለት ወጣት ኦርቶዶክሳውያን ላይ ዘግናኝ ግድያ መፈጸሙ ተሰምቷል።

#በሚታና ዋጂ ቀበሌ የተፈጸመው ግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ ወጣቶቹ መኖሪያ ቤት የገቡት ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር ካዋሏቸው በኋላ ወደሚታና ጋዶ ቀበሌ በመውሰድ፣ አንደኛውን በስለት አርደው፣ ሁለተኛውን ደግሞ በጥይት በመምታት በጭካኔ ገድለዋቸዋል።

#የወጣቶቹ ሥርዓተ ቀብር ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በጋዶ ማሕደረ ስብሐት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን፣ ምዕመናንና በቤተሰብ በተገኘበት በአንድ መቃብር ተፈጽሟል።

#በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በአገልጋዮችና ምእመናን ላይ በተደጋጋሚ ለሚፈጸመው የክርስቲያኖች ጥቃትና ግድያ ከየትኛውም አካል መፍትሔ አልተሰጠውም።

EOTC MK TV

#የአባቶቻችን ዝምታ እስከ መቼ? በቤተክህነቱ ከፍታ ላይ የተቀመጣችሁ መሪዎች ጳጳሳትና አባቶች ሆይ! መቼ ነው የምትናገሩት? መቼ ነው የምትተነፍሱት?

መሪነታችሁና አባትነታችሁ ለበጎች ጥበቃ ካልሆነ...

የምዕመናን እምባና ሞት ካላሳዘናችሁ...

ወጥታችሁ ለግፉአን ድምፅ ካልሆናችሁና "በቃ!" ካላላችሁ... የአባትነታችሁ ትርጉም ምንድነው?

ሁላችንም ልናውቀው የሚገባ እውነት፦ ዛሬ በሩቅ የምንሰማውና የለመድነው የሞት ዜና ነገ እያንዳንዳችን ቤት ማንኳኳቱ የማይቀር እውነታ ነው!

ማንም በተራው ሳይታ,ረድ የሚያመልጥበት ምድር ላይ አይደለንም።

አሁኑኑ እንነጋገር በአንድነት እንቁም!

ከእንግዲህ ዝምታ ፈራጅ ነው!

ሁላችንም ተቀራርበን ስለ መፍትሔው ልንወያይ በቁጭት ልንነሳና ኦርቶዶክሳውያን በአንድነት ልንቆም ይገባል።

የአባቶቻችን እምነትና የንፁሃን ደም በታሪካችን ፊት ይፋረደናል!

ዝምታችን ይብቃ!

"የሞታችን ዜና የዕለት ተዕለት ወሬአችን ሊሆን አይገባም!"

02/06/2026

#ዘወትር ዐርብ የጌታችን ሕማማት እያሰበ ስጋውን በመከራ እየጎዳ ኖሯል

#በሃገራችን በኢትዮጵያ በስማቸው የታነጹ 3ት ታላላቅና ጥንታዊ ገዳማት አሏቸው፡፡ ከማዕድ በኋላ ስብሐት ተብሎ ስማቸው ተጠርቶ መጉረስ ሙታንን እንደሚያስምር ቃል ኪዳን የተሰጣቸው አባት ናቸው አባ ቡላ ወይም አቡነ አቢብ፡፡

#በሊቀ ሰማዕታት በቅዱስ ጊዮርጊስ ዘመን የነበሩና ሰማዕትነት የተቀበሉአባት ሲሆኑ፣ ቡላ ማለት የእግዚአብሔር አገልጋይ፣ አቢብ ደግሞ የብዙዎች አባት፣ የመልካም ሥራ ሁሉ ባለቤት ማለት ነው፡፡

#ገድላቸው “የተከበረ አባት፣ በትሩፋት የተጋ” የመልካም ነገሮች ሁሉ አባት፣ ይላቸዋል፡፡ የተውለዱት በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ በሮም ሉፊ በሚባል አውራጃ የካቲት 16 ነው፡፡ እጅግ ጽኑዕ ክርስቲያኖች የነበሩት ወላጆቻቸው ልጅ አልነበራቸውም፡፡

#በዘመነ ሰማዕታት ከመክስምያኖስ ሸሽተው በበረሃ ሳሉም በመልአክ ብሥራት ቡላን ቢወልዱም ዘመነ ሰማዕታት በመሆኑ ለአንድ ዓመት ሳይጠመቅ ቆይቶ በእመቤታችን ትዕዛዝ የሮሙ ሊቀ ዻዻሳት አባ ሰለባስትርዮስ በረሃ ወርዶ አጥምቆታል፡፡

#ሊያጠምቀው ሲል ሕፃኑ ቡላ ተነስቶ እጆቹንም ዘርግቶ "አሐዱ አብ ቅዱስ፣ አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ ውዕቱ መንፈስ ቅዱስ" ብሎ አመስግኖ ተጠመቀ፡፡ ከሰማይም ሕብስትና ጽዋዕ ወርዶላቸው ሊቀ ዻዻሳቱ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው፡፡ ሕፃኑንም "ቡላ" ብሎ ሰየመው፡፡

#ወላጆቹ ገና በ10 ዓመቱ ተከታትለው ስላረፉ ጎረቤቶች አሳድገውታል፡፡ ሃገረ ገዢው ለጣዖት ስገዱ ብሎ አዋጅ ባስነገረ ጊዜ በሕፃን አንደበቱ አምልኮተ ክርስቶስን ሰበከ፡፡ ሃገረ ገዢውም ተበሳጭቶ ስፍር ቁጥር በሌለው መከራና ስቃይ ገደለው፡፡

#ኃይለ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበርና ከሞቶ አስነሳው፡፡ ቅዱስ ቡላ ወደ ሌላ ከሃዲ መኰንን ዘንድ ሄዶ ስለአምልኮተ ጣዖቱ ገሠጸው፡፡ ያም ከሃዲ መኰንን ብዙ ካሠቃየው በኋላ ሚያዝያ 18 ቀን ራሱን በሰይፍ አስቆረጠው፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም ለ2ኛ ጊዜ ከሰማይ ወርዶ ቅዱስ ቡላን ከሞት አስነሣው፡፡

#ወደ አንድ ገዳምም ወስዶ በምንኩስና እንዲኖር መታዘዙን ነገረው፡፡ አባ ቡላ ወደ በርሃ ከገባ ጀምሮ ዘወትር ዐርብ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን፣ የመድኀኔ ዓለምን ሕማማት እያሰበ ስጋውን በተለያየ መከራ እየጎዳ ኖሯል፡፡

#ምንም ነገር ሳይቀምስ፤ መዝሙረ ዳዊትን እየጸለየ ለ42 ዓመታት ጹሟል፡፡ ጌታችን ተገልጦለት “ከእንግዲህ ስምህ ቡላ አይሁን አቢብ ተባል እንጂ የብዙዎች አባት ትሆናለህ” አለው፡፡

#አቡነ አቢብ ታላቁ አባ ዕብሎይን ጨምሮ በርካታ ደቀ መዛሙርትን አፈራ፡፡ ከእመቤታችን ጋርም ዕለት ዕለት ይነጋገር ነበር በተጋድሎ ሕይወቱም ከ10 ጊዜ በላይ ሙቶ ተነስቷል፡፡ ከዚህ ዓለም ድካም ሲያርፍም ገዳሙ በመላእክት ተሞላ፡፡

#ሰው ቢረሳ ቢረሳ ምግቡን አይረሳምና “በእንተ አቡነ አቢብ” ስለ አባ ቡላ ብሎ በሚመገብ ጊዜ ያሰበውን ማርልኝ ብለው የለመኑትን ልመና አምላካችን ተቀብሎላቸው ዛሬም በዚህ በቃል ኪዳናቸው የሚያስምሩ ሆነዋል፡፡

#የጻድቁ አቡነ አቢብ ረድኤትና በረከት አይለየን፡፡

01/06/2026

❖የጌታችንን አብነት ተከትለው...

❖ቅዱሳን ሐዋርያትን ለተልዕኮ የጠራቸውና ዓለምን በወንጌል ብርሃን እንዲያበሩ የመረጣቸው ጌታችን ግን ለድካማቸው አሳልፎ አልሰጣቸውም፡፡

❖ ከትንሣኤው በኋላ እስከ ዕርገቱ ድረስ ለ40 ቀናት እየተገለጠላቸው እምነታቸውን አጸናላቸው፤ ቅዱስ ቃሉን አስተማራቸው፤ ለሐዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያንም መሰረት የሆነ መንፈሳዊ ሥርዓትን አሳያቸው፡፡

❖ ስለ ስሙ መከራን ለመቀበል እንዲጸኑ የሚያጸና መንፈስ ቅዱስ ያስፈልጋቸው ነበርና “እኔ የአባቴን ተስፋ ለእናንተ እልካለሁ፤ እናንተ ግን ከአርያም ኃይልን እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ተቀመጡ፡፡” በሉቃስ 24÷49 በማለት ተስፋ ሰጣቸው፡፡

❖ ይህም ተስፋ አስቀድሞ በነቢያት የተነገረ ነው፡፡
ቅዱሳን ሐዋርያት በጽርሐ ጽዮን ተሰብስበው ሳሉ መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል ወርዶ ሰማያዊ ሀብትን፣ ዕውቀትና ጸጋን አድሏቸዋል፡፡

❖ መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላም በአእምሮ ጎልምሰዋል፤ ቈራጦች፣ ጽኑዓን ሆነዋል፡፡ ለስብከተ ወንጌል የሚፋጠኑበትንና ለሰማዕትነት የሚዘጋጁበትን ልቡናም ታድለዋል፡፡

❖ ከዚህ ቀን ማግስትም ጀምረውም እስከ ሐምሌ 5 ድረስ ቅዱሳን ሐዋርያት በጾም አሳልፈዋል።

❖ ይህ ጾም ከቤተ ክርስቲያናችን የአዋጅ አጽዋማት ውስጥ አንዱ ሲሆን ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታችንን ምሣሌ አድርገው የጾሙት ጾም ነው።

❖ የሰኔ ጾም ይህ ጾም የሐዋርያት ጾም በመባል ይታወቃል ስለ ምን የሐዋርያት ጾም ተባለ ቢሉ በበዓለ ጰራቅሊጦስ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ የጾሙት ጾም ስለሆነ ነው።

❖ የሰኔ ጾም ቢያንስ 15 ቢበዛ 45 ቀናት ያህል ይጾማል። የሰኔ ጾምን እስከ 9 ሰአት እንድንጾም ቤተክርስቲያን አውጃለች። ጾሙ የሚገባበት ቀን በየዓመቱ የተለያየ ቢሆንም የጾሙ ማብቂያ ዕለት ግን ሐምሌ 5 ድረስ ነው ።

❖ ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታችን ህሙማነ ሥጋን በተዓምራት ሕሙማነ ነፍስን በትምህርት ከማዳኑ አስቀድሞ በገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ 40 ቀን 40 ሌሊት እንደጾመና እንደጸለየ ሁሉ ቅዱሳን ሐዋርያትም መጀመሪያ አብነቱን ተከትለው ጾመዋል፡፡

❖ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ዓለምን ዕጣ ተጣጥለው (ተከፈፍለው) ዞረው ከማስተማራቸው አስቀድመው የሥራቸው መጀመሪያ ጾምን አድርገዋል፡፡

❖ ጾሙን የበረከት ያድርግልን በሰላም ያስፈፅመን አሜን።

Photos from Rebuni ረቡኒ's post 31/05/2026

ጊዮርጊስ ኃያል፣ ኃያል መስተጋድል
ገባሬ ተአምር፣ ኮከበ ክብር

30/05/2026

ትልቁ ይሕይወት አጥር

Photos from Rebuni ረቡኒ's post 30/05/2026

#አይእቲ ዛቲ እንተ ታስተርኢ እምርሁቅ ከመ ማህቶት ደብረ ገነት
- ሙሴኒ ርዕያ ሀገር ቅድስት፣ ዕዝራኒ ተናገራ፣ ዘመራ ዳዊት

#ያቺ ከርቀት እንደ ፋና የምታበራ የገነት ተራራ ናት
- ሙሴ ያያት ቅድስት ሀገር፣ ዕዝራ የተናገረላት፣ ዳዊትም የዘመረላት ናት

#ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 25 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ ለክርስቲያን፣ ለአይሁዳዊያንና ለእስላሞች ሁሉ ተገልጻ ትታይ ነበር።

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Website

Address


Addis Ababa