Armauer Hansen Research Institute

Armauer Hansen Research Institute

Share

The Armauer Hansen Research Institute (AHRI) was founded in 1970.

Photos from Armauer Hansen Research Institute's post 23/06/2026

“ጠንካራ ተቋም ለጠንካራ አገረ መንግሥት!”
-----------------------------------
የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (አህሪ) መላው አመራሮችና ሠራተኞች “በምርጫ ማግስት፤ ጠንካራ መንግሥት” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ የውይይት አካሂደዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የአህሪ ዋና ዳይሬክተር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታመነ አጫሞ የ7ኛውን አገራዊ ምርጫ አጠቃላይ ሂደት ቅድመ ምርጫ፣ የምርጫ ወቅት እና ድኅረ ምርጫን የሚዳስስ እንዲሁም ጠንካራ አገረ መንግሥትን ለመገንባት የተቀመጡ ዓላማዎችን የሚያብራራ ዝርዝር የመነሻ ሰነድ አቅርበዋል።

የአህሪ ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ዘላቂና ጠንካራ መንግሥት ለመገንባት ጠንካራ ተቋማት መሠረታዊ ሚና እንደሚጫወቱ አስገንዝበዋል።

አህሪ በጤናው ዘርፍ የጥናትና ምርምር ሥራዎች ላይ ከፍተኛ ሚና የሚጫወትና ለሀገር እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ ያለው ተቋም መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የተቋሙን ተፅዕኖና አበርክቶ ይበልጥ ለማጠናከር እያንዳንዱ ሠራተኛ የበኩሉን ኃላፊነት በብቃትና በቁርጠኝነት መወጣት እንዳለበት ገልጸዋል።

ፕሮፌሰር አፈወርቅ አክለውም፣ ኢንስቲትዩቱ እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ የበለጠ ለማሳደግ እና በሕክምናና በመድኃኒት ዘርፍ ራስን በመቻል አገራዊ ሉዓላዊነትን ለማጠናከር፣ የምርምር ውጤቶችን ወደ ተግባራዊ ምርትና ፈጠራ ለመቀየር በትጋት መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በቀረበው የመነሻ ሰነድ ላይ በተካሄደው ሰፊ ውይይት፣ 7ኛው አገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ እና የሀገርን ዘላቂ ጥቅም ያስቀደመ ሂደት በመሆኑ፣ ለኢትዮጵያ ታሪካዊ ስኬት ያስመዘገበ ምዕራፍ መሆኑ ተጠቅሷል።

በመጨረሻም፣ የተጀመረውን የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እና የዜጎችን ፍላጎትና ተሳትፎ መሠረት ያደረገ ጠንካራ መንግሥት ለመገንባት፣ እያንዳንዱ የተቋም ሠራተኛ የዕለት ተዕለት ሥራውን በታማኝነት፣ በብቃት እና በኃላፊነት መፈጸም ወሳኝ መሆኑ በመድረኩ ላይ ተገልጿል። ውይይቱም በአንድነት በግል ጠንካራ የስራ ባህል÷ ጠንካራ ተቋም እና ጣንካራ መንግስት ለበለጸገች ሀገር ወሳኝ መሆኑ ላይ ግንዛቤ በመያዝ በቁርጠኝነት በስኬት ተጠናቋል።

LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/106861043/admin/dashboard/
Website:
https://ahri.gov.et/
Facebook: https://web.facebook.com/AHRIGovEt/?_rdc=1&_rdr #
Youtube: https://www.youtube.com/
Telegram:
https://t.me/ahriethiopia

Photos from Armauer Hansen Research Institute's post 22/06/2026

የካሳቫ ስታርች ለፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ

በአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት በጥናት አዋጭነቱ የተረጋገጠውንና ለፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ግብዓት የሚውለውን የካሳቫ ስታርችን ጥናት ከኢንቨስተሮችና ከኢንቨስትመንት ጋር ማገናኘት ይቻል ዘንድ የመጀመሪያው የውይይት መርሃ ግብር ተካሄደ።

ውይይቱ የተከናወነው በአህሪ እና በኦሞአዲስ አግሪፕላትፎርም (OmoAddis AgriPlatform plc) መካከል ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም በኢንስቲትዩቱ የተጠናውን የአዋጭነት ጥናት ከኢንቨስተሮችና ከኢንቨስትመንት አማራጮች ጋር በማገናኘት ወደ ተግባራዊ ምርት ማሸጋገር ነው።

በዚህ ስልታዊ የውይይት መድረክ ላይ የኦሞአዲስ አግሪፕላትፎርም መስራችና ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኤርሲዶ ላንዴቦ፣ የአህሪ ዋና ዳይሬክተር ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ፣ የአህሪ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ መሳይ ወ/ማርያም እና የፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የሁለቱ ተቋማት አመራሮች ያሉትን መልካም ዕድሎች በመጠቀም በቀጣይ በጋራ መሠራት ስላለባቸው ተከታታይ ስራዎችና ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎች ላይ መግባባት ላይ ደርሰዋል። ይህ ትብብር የሀገር ውስጥ የመድኃኒት ማምረቻ ግብዓቶችን በራስ አቅም ለመተካት ትልቅ እምርታ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።

LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/106861043/admin/dashboard/

Website:
https://ahri.gov.et/

Facebook: https://web.facebook.com/AHRIGovEt/?_rdc=1&_rdr #

Youtube: https://www.youtube.com/

Telegram:
https://t.me/ahriethiopia

Photos from Ministry of Health,Ethiopia's post 21/06/2026
Photos from ALERT Comprehensive Specialized Hospital's post 19/06/2026
19/06/2026

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የፓንደሚክ ፈንድ የቦርድ ተባባሪ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ
__________

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የፓንደሚክ ፈንድ የበላይ ቦርድ ተባባሪ ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።

የፓንደሚክ ፈንድ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸዉ አገራትን አቅም በመገንባት ድንገተኛ የጤና አደጋ ክስተቶችን ለመከላከል፣ ለመለየትና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እንዲቻል በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተቋቋመ መሊቲላተራል ፋይናንሲንግ አሰራር ሲሆን ሚኒስትሯ በአዲሱ ኃላፊነታቸው ዓለም አቀፍ አጋርነቶች እንዲጠናክር እና አገራት ወረርሽኞችን ለመከላከል ለሚያደርጉት ኢንቨስትመንት የሚሰጠውን ድጋፍ በበላይነት በመምራት ለዉጥ እንደሚያመጡ ፈንዱ ያለዉን እምነት ገልጸዋል፡፡

ዶ/ር መቅደስ ኃላፊነቱን የተረከቡት ከሩዋንዳ ጤና ሚኒስትር ከሆኑት ከዶ/ር ሳቢን ንሳንዚማና ሲሆን፣ ሚኒስትሯ ባስተላለፉት መልዕክት የህብረተሰባችንን ህይወት መታደግ የሚችልና የዓለምን የጤና ደህንነት ዋስትናን የሚያረጋግጥ ጠንካራ የጤና ስርዓት በመገንባት ለትዉልድ ማስተላለፍ አለብን ብለዋል።

Minister of Health Dr. Mekdes Daba elected as Co-Chair of the Pandemic Fund Board
____________

Minister of Health Dr. Mekdes Daba has been elected as a Co-Chair of the Pandemic Fund Governing Board.

The Pandemic Fund is a multilateral financing mechanism established by the global community to help build capacity in low- and middle-income countries to prevent, detect, and respond rapidly to public health emergencies. The Fund expressed its confidence that, in her new role, the Minister will bring about change by overseeing the strengthening of international partnerships and the support provided for investments made by countries to prevent pandemics.

Dr. Mekdes took over the responsibility from Dr. Sabin Nsanzimana, the Minister of Health of Rwanda. In her message, the Minister stated that we must build and pass on to future generations a strong health system that can save the lives of our society and ensure global health security.

Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

Photos from Armauer Hansen Research Institute's post 19/06/2026

በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት እና በአህሪ መካከል የኮሙዩኒኬሽን ስራዎች የልምድ ልውውጥ ተካሔደ

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የኮሚኒኬሽን የስራ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች የአመራርና የሙያ አቅማቸውን ለማሳደግ እንዲሁም የተቋማትን የመረጃ ፍሰትና ግንኙነት ይበልጥ ቀልጣፋ ለማድረግ በአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (አህሪ) የስራ ጉብኝትና የልምድ ልውውጥ አካሄዱ።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ በልምድ ልውውጡ መርሀ ግብር ተገኝተው እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የተቋማቸውን ልምድ ያካፈሉ ሲሆን በቀጣይም ከኮልፌ ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ጋር በጋራ ተቀናጅተው በመስራት የማህበረሰቡን የመረጃ ተደራሽነት ለማስፋት በትኩረት አንደሚሰራ ተናግርዋል ።

የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ምርምር ሀይሌ በበኩላቸው የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (አህሪ) በርካታ የምርምር ውጤቶች ውጤታማ በሆነ መንገድ በማምረት ለሀገር የሚተርፍ ስራ እያከናወነ መሆኑን ገልፀው በቀጣይም በጋራ ልምድ በመውሰድና ተባብሮ በመስራት ተቋሙ ለማህበረሰቡ ለማስተዋወቅ ጠንካራ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ስራዎች ይሰራሉ ብለዋል።

ይህ የልምድ ልውውጥ የህዝብ ግንኙነትና የኮሚኒኬሽን ስራዎችን በቴክኖሎጂ በመደገፍ፣ ወቅታዊና ተዓማኒ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የሚከናወኑ ተግባራትን እና የጋራ የእርስ በእርስ ግንኙነትን ለማጠያከርና በቀጣይ በጋራ ለመስራት ታሳቢ ያደረገ ነው።

በጉብኝቱና በልምድ ልውውጡ ወቅት የክፍለ ከተማው የኮሚኒኬሽን አመራርች፣ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች በአህሪ እየተከናወኑ ያሉ የዲጂታል ሚዲያ አጠቃቀም፣ የኮንቴንት (ይዘት) ዝግጅት፣ የሚዲያ ክትትልና ትንተና እንዲሁም የስራ አካባቢ አደረጃጀቶችን በቅርበት ተመልክተዋል። በተለይም ውስብስብ የሆኑ የምርምርና የሳይንስ መረጃዎችን ለሰፊው ህብረተሰብ በተሻለ ጥራት፣ ቀላልና ሳቢ በሆነ ይዘት ማስተዋወቅ በሚቻልባቸው ስልቶች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

በመጨረሻም የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የኮሚኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች ከዚህ ጉብኝት ያገኟቸውን ጠቃሚ አሰራሮች ወደ ስራ በመቀየር፣ በቀጣይም ከተቋሙ ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/106861043/admin/dashboard/
Website:
https://ahri.gov.et/
Facebook: https://web.facebook.com/AHRIGovEt/?_rdc=1&_rdr #
Youtube: https://www.youtube.com/
Telegram:
https://t.me/ahriethiopia

Photos from Armauer Hansen Research Institute's post 19/06/2026

ምርምርና ሚዲያ ለላቀ ጤና

የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (አህሪ) "ምርምርና ሚዲያ ለላቀ ጤና" በሚል መሪ ሐሳብ ያዘጋጀውን 4ኛውን ዓመታዊ የሚዲያ ፎረምና የምርምር ማዕከላትን ጉብኝት በስኬት አካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ ላይ ከተለያዩ የሚዲያ ተቋማት የተወጣጡ ጋዜጠኞች፣ የጤና ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት የኮሙኒዩኬሽን ሀላፊዎች እና ባለሙያዎች የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የሁሉም ወረዳዎች የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊዎች፣ የተሳተፉ ሲሆን በኢንስቲትዩቱ ውስጥ የሚገኙ ዘመናዊ የምርምር ላቦራቶሪዎች እና በውስጡ የሚገኙ የተለያዩ ቤተ ሙከራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ባደረጉት ንግግር "የጤና ምርምር ጉዳይ ከማኅበራዊና ከኢኮኖሚያዊ አልፎ ከሀገር ሉዓላዊነት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ያሉ ሲሆን፣ የሚዲያ ተቋማት የምርምር ውጤቶችን ተፅዕኖ ለማስፋት ከተቋሙ ጋር አብረው እንዲሠሩም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዓለምሰገድ አብዲሳ፣ በኢንስቲትዩቱ ስለሚሰሩ ስራዎች በገለፁበት ወቅት የጤና ዘርፍ ምርምርን ለየት ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ እንደ ወረርሽኝ ያሉ የሚያጋጥሙ ችግሮችም ሆኑ በዘርፉ የሚገኙ የምርምር ውጤቶች ዓለም አቀፋዊ ተፅዕኖ ያላቸው መሆኑ ነው። ስለሆነም አህሪ የሚያገኛቸው የምርምር ውጤቶች ጥቅማቸው አገራዊ ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፋዊ ፋይዳ አለው ብለዋል።

የኢንስቲትዩቱ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒዩኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ደጅይጥኑ ሙላው ምርምር እና ሚዲያ በሚል ርእስ የተቋሙን የኮሚኒዩኬሽን እና ሚዲያ ስራዎችን እና ተግባራትን እንዲሁም የተከናወኑ ስራዎች ላይ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን የፎረሙ ዋና ዓላማ በምርምርና በሚዲያ መካከል ጠንካራ ድልድይ በመፍጠር ሳይንሳዊ ግኝቶችን ለኅብረተሰቡ ፈጣንና ጥራት ባለው መንገድ ማድረስ መሆኑን በመግለፅ ሚዲያዎች ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው አስታውሰዋል፡፡

በእለቱም ከየተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች እና ከሚዲያ ባለሙያዎች ጋር በምርምርና በሚዲያ አጋርነት ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት ተካሂዷል። በውይይቱ የጤና ምርምር ከሀገር ሉዓላዊነትና ደኅንነት ጋር በቀጥታ የተቆራኘ በመሆኑ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል የተባለ ሲሆን በመሆኑም እነዚህ የሆኑ የምርምር ውጤቶች ተገቢውን አዎንታዊ ተፅዕኖ ማምጣት እንዲችሉ የሚዲያ ተቋማት ከኢንስቲትዩቱ ጋር በቅንጅትና በባለቤትነት ስሜት በጋራ ሊሠሩ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/106861043/admin/dashboard/
Website:
https://ahri.gov.et/
Facebook: https://web.facebook.com/AHRIGovEt/?_rdc=1&_rdr #
Youtube: https://www.youtube.com/
Telegram:
https://t.me/ahriethiopia

Photos from Ethiopian Broadcasting Corporation's post 18/06/2026
Photos from DireTube's post 18/06/2026
Photos from Amanuel mental specialized hospital's post 18/06/2026
Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address


Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00