Bright Future - Melkam Yihonal

Bright Future - Melkam Yihonal

Share

በብዙ ልፋት ውስጥ ጥቃቅን ጉድለቶች ቢኖሩም በርካታ መልካም ውጤቶች ግን እየተመዘገቡ ነው። ዋናው እኔ/አንቺ/አንተ በጎ አስተዋጽኦ ይኑረን፤ አመስጋኝ እንሁን። ያኔ የጎደለውን እንሞላለን።

Photos from Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ's post 09/06/2026
Photos from Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ's post 08/06/2026

ሁሌም የተናገሩትን መኖር!!

Photos from Mayor Office of Addis Ababa's post 07/06/2026

Addis Ababa: Week in Review

06/06/2026

ባለፉት ጥቂት ዓመታት በአዲስ አበባ የተከናወነው የልማት ስራ በሚታዩ መሰረተ ልማቶች መስፋፋት ላይ ብቻ ያተኮረ ሳይሆን በዓይን የመታየት እድላቸው ውስን ቢሆንም የነዋሪውን ህይወት የቀየሩ በርካታ አንኳር ውጤቶች የተመዘገቡበት መሆኑን የሚተነትን እና ዛሬ የታተመ ጽሑፍ ነው። ለውጦቹ የራዕይና የተግባር ድምር ውጤቶች ሲሆኑ ለመሰረተ ልማት መስፋፋትም ቢሆን ያበረከቱት አስተዋጽኦ ተካትቷል።
መልካም ንባብ!!

05/06/2026
Photos from Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ's post 05/06/2026

Great milestone!!

Photos from Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ's post 04/06/2026

ለአፍታ የማይቆም ለውጥ፣ በውጤት የታጀበ ጥረት!!

03/06/2026

ራዕይና የህዝብ እምነት
*******************
ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የሀገሪቱን የቀጣይ አምስት ዓመታት እጣ ፈንታ የሚወስን ሀገራዊ ምርጫ በተካሄደበት ማግስት ግንቦት 25 በማለዳ የሀገሪቱና የአዲስ አበባ ከተማ አመራሮች እንጦጦ ላይ ተከስተው ነበር። ጫና ሳይበግረው ህዝቡ እስከ እኩለ ሌሊት በመጠበቅ ዴሞክራሲያዊ መብቱን ለመተግበር ያሳየውን ቁርጠኝነት በማድነቅ ያመሰገኑት ጠ/ሚ/ር አብይ እና ከንቲባ አዳነች ህዝቡን ለመካስ የጀመሩትን ስራ ለማስቀጠል ሰበብ ፈልገው ጊዜ ማባካን ተገቢ ባለመሆኑ ነው እዛ የተገኙት። በውጤቱም ለከተማዋም ሆነ ለህዝቡ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለውን የወንዝ ዳርቻ ልማት መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።

በመሰረቱ እነዚህ ሁለቱ መሪዎች ለሚባክን ጊዜ ምንም ጊዜ እንደሌላቸው አብረዋቸው የሰሩ ባልደረቦቻቸውና የስራቸው ውጤት ምስክሮቻቸው ናቸው። ለሚሰሩት ስራ የሰዓት ገደብ የላቸውም፣ ቀን ብቻ ሳይሆን ማታም መደበኛ የስራ ሰዓታቸው ነው። የነበረ አሰራር ከውጤታማነት እንዲጎትታቸው አይፈቅዱም፣ ቀልጣፋና ዘመናዊ አሰራር እውን ማድረግ መርሃቸው ነው። ለጊዜያዊና ወቅታዊ ውዳሴም ሆነ ኩነኔ ጆሮ የላቸውም፣ በምስጋናም ሆነ በእርግማን ከትልቁ መዳረሻቸው እንደማይጎድሉ ተረድተዋል።

እኔ ግን እላችኋለሁ የእነዚህ መሪዎች ትጋት ገፊ ምክንያት ራዕያቸው ነው፣ የእነዚህ መሪዎች ትጋት ገፊ ምክንያት የህዝቡ እምነት ነው። ድህነትን፣ ጉስቁልናን፣ ኋላ ቀርነትን በመፀየፍ፣ የበለፀገችና ተወዳዳሪ ሀገር እውን የማድረግ ራዕይ የትጋታቸው መሰረታዊ ጉልበት ነው። በብዙ እልህ አስጨራሽ ተግዳሮት ውስጥ ቢያልፉም ከስምንት ዓመት በፊት ያዩት እና ዛሬም ህዝቡ በእነርሱ ላይ ያለው የፀና እምነት ለትጋታቸው ተጨማሪ ጉልበት ሆኗቸዋል።

ማህበራዊ ፍትህ የሰፈነባት፣ የበለፀገች፣ ተወዳዳሪና የዜጎችዋ ክብር የተመለሰላት ሀገር እውን እስኪያደርጉ ድረስ እረፍት እንደማይኖራቸው ሰርተው ያመጡት ውጤት ብቻ ሳይሆን ለነገ የሚናገሩት ቃልና የሚገቡት ተስፋ ይመሰክራል። ተናግረው ማድረግን በተግባር ያሳዩ መሆናቸው ደግሞ ራዕያቸውን ለመደገፍና ቃላቸውን ለማመን ምክንያት ይሆናል።

መልዕክት አለኝ:- ራዕያቸው፣ ትጋታቸውና ቁጭታቸው የገባን ቀኝ እጃችንን እንስጣቸው፤ በሌቦች፣ በጽንፈኞችና በስልጣን ጥመኞች ሴራ የተጠራጠርናቸው ደግሞ ረጋ ብለን በስራቸው እንመዝናቸው። ደግሜ የገባኝን እላለሁ እነዚህ መሪዎች መዳረሻቸውን ከመነሻቸው አይተው የተነሱ ናቸውና ራዕያቸውን ሳያሳኩ ለመቆም፣ ለማረፍ፣ ተስፋ ለመቁረጥ ሀሳብም ጊዜም አይኖራቸውም።

ተፃፈ በይመጣል ባህሩ

Photos from Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ's post 03/06/2026

ድንቅ ውጤት!!

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Website

Address


Addis Ababa