03/05/2026
በጋርዳ ማርታ ወረዳ ግብርና ጽ / ቤት የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ
Garda Marta Woreda
03/05/2026
19/04/2026
14/04/2026
06/04/2026
በጋሞ ዞን በገረሴ ዙሪያ ወረዳ የ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ የሆነው የቡና ችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ።
የጋሞ ዞን የግብርና መምርያ ከፊተኛ አመራሮች በዳንብሌ ኦሳ ቀበሌ ተገኝተው ተከላውን አስጀምሯል።
#መጋቢት 28/2018 ዓ.ም (ጋሞ ዞን ግብርና ኮሙኒኬሽን)
በጋሞ ዞን በገረሴ ዙሪያ ወረዳ የ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ የሆነው የቡና ችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ ፕሮግራም በዳንብሌ ኦሳ ቀበሌ አቦይ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ተካሄደ።
በተከላው ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ የጋሞ ዞን የግብርና መምርያ ም/ኃላፊ አቶ ወርቅነህ ካልሳ ባስተላለፉት መልዕክት የ2018 የአርንጓዴ አሻራ አካል የሆነ የቡና ተከላ እንደ ጋሞ ዞን 8.2 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል መታቀዱን አስታውቋል።
እንደጋሞ ዞን ከ24 ሽህ ሄ/ር በላይ መሬት ላይ ቡና እየለማ የሚገኝ ሲሆን ከ15 ሽህ ሄ/ር በላይ ምርት እየሰጠ እንደሚገኝ አስታውቋል።
ይኸ ደብር ለቡና ምርት ምቹ ቦታ በመሆኑ ልንጠቀምበት እና ልናሳድግ ይገባል ብሏል።
የጋሞ ዞን የግብርና መምርያ የሻይ ቡናና ቅመማ ቅመም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሻምበል ቦኩ በበኩላቸው ቡና በሀገራችን ከሚለሙ ሰብሎች ትልቁን ቦታ የሚይዝና ከፊተኛ የውጪ ምንዛሪ የሚያስገኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በዚህ ዓመት የቡና ተከላ ከአሬንጓዴ አሻራ ጋር አስተሳስረው ለማልማት ስትራቴጂ መነደፉን ገልጸው ትኩረት ልንሰጥ የሚገባን በክላስተርም በመደበኛውም የሚሠሩ ሥራዎች ከአረንጓዴ አሻራ ጋር አስተሳስሬን መሥራት አለብን ብሏል።
ይህ ቦታ ለተሞክሮ ልሆን የሚችል በመሆኑ በደብሩ አካባቢ ያሉትን አርሶ አደሮችን አስተሳስሮ ልቀጥል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የገረሴ ዙሪያ ወረዳ የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ጎንደሬ ጉራራ የቡና ምርትና ምርታማነት ለመጨመር ቡናን በሙሉ ፓኬጅ ልለማ እንደሚገባ አሳስቧል።
እየለማ ያለው ቡና በሙሉ ፓኬጅ እየለማ ባለመሆኑ በቂ ምርት እየሰጠ አለመሆኑን ገልጸው ፓከጁን ካላሟላን የሚጠበቀውን ምርት ልናገኝ አንችልም ብሏል።
የገረሴ ዙሪያ ወረዳ የግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር አዳኔ ደስታ በበኩላቸው በገረሴ ዙሪያ ወረዳ ቡና አልሚ ከሆኑ 15 ቀበሌያት አንዷ ወደሆነችው ዳንብሌ ኦሳ ቀበሌ እንኳን ደህና መጣችሁ ብሏል።
በገረሴ ዙሪያ ወረዳ 5337 ሄ/ር መሬት ላይ ቡና እየለማ የሚገኝ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 4609 ሄ/ር መሬት ቡና ምርት እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።
የደንብሌ ኦሳ አቦይ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አስተዳዳሪ ቄስስ ሐብተማርያም ደለለኝ እንደገለጹት መንግስት የደብሩ አካባቢ እንድለማና አሬንጓዴ እንድለብስ እያደረገ ላለው ድጋፍ እና ከጋሞ ዞን ግብርና መምርያና ከገረሴ ዙሪያ ወረዳ አመራሮችና ባለሚያዎች እዚህ ተገኝታችሁ የወረዳዊ የቡና ተከላ ማስጀመሪያ ፕሮግራም በማካሄዳቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው ምሥጋና አቅርቧል።
ከዚህ ቀደም የGIZ ግብረ ሰናይ ድርጅት ከገረሴ ዙሪያ ወረዳ ጋር በመተባበር በአፈር ጥበቃና በአሬንጓደ አሻራ በተሠራ ሥራ ዛሬ ደብሩ በአሬንጓደ የደመቀ ሲሆን አሁን ከአንድ ሄ/ር በሚበልጥ መሬት ላይ ቡና እንዲለማ መንግስት እያደረገ ላለው ድጋፍ አመስግነዋል።
24/03/2026
18/03/2026
"በክልሉ የሌማት ትሩፋት ኢንሼቲቭ ግቦችን ማሳካት የሚችል ሠራዊት እየተገነባ ነው!" አባይነህ ኬዳ (ዶ/ር)
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ከወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ ጋር በመተባበር ለቀበሌ የእንስሳት እርባታ እና የእንስሳት ጤና ልማት ጣቢያ ባለሙያዎች ያዘጋጀው የተግባርና የንድፈ-ሀሳብ አቅም ግንባታ ስልጠና ተጀምሯል።
የክልሉ ግብርና ቢሮ ከወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ ጋር በመተባበር ለክልሉ የእንስሳት እርባታና የእንስሳት ጤና የልማት ጣቢያ ባለሙያዎች ያዘጋጀውን በተግባር የተደገፈ የንድፈ-ሀሳብ ስልጠና በወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ እየሰጠ ይገኛል።
የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ አባይነህ ኬዳ (ዶ/ር) መድረኩን በከፈቱበት ወቅት እንደገለፁት የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ሀሳብ አፍላቂነት ተጀምሮ እየተተገበረ የሚገኘውን የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ ለማሳት ሁሉ-አቀፍ ርብርብ እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል።
የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ የግብርና ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ መሆኑን የጠቆሙት ምክትል የቢሮ ኃላፊው በወተት፣ በሥጋ፣ በዶሮና ዕንቁላል፣ በዓሣ፣ በማርና በሀር ልማት የትኩረት መስኮች መንደርን መሠረት በማድረግ የተከናወኑ ተግባራት ዕምርታ እየተመዘገበ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
የእንስሳት ምርታማነት የሚረጋገጠው የዘርፉ ምሰሶ የሆኑት የዝርያ ማሻሻል፣ የመኖ ልማትና አጠቃቀም እንዲሁም መከላከልን መሠረት ያደረገ የእንስሳት ጤና አገልግሎቶች ሲታገዝ መሆኑን ያነሱት ዶ/ር አባይነህ ሶስቱንም ምሰሶዎች በውጤታማነት ለመተግበር የሌማት ትሩፋት ሠራዊት እየተገነባ ይገኛል ብለዋል።
በቀበሌ ደረጃ ለአርሶና አርብቶ አደሩ የሚሰጠውን አገልግሎት ውጤታማ ለማድረግ ባለሙያው በጥናት በተለዩ የክህሎት ክፍተቶችን የሚሞሉ በተግባር የተደገፈ የንድፈ-ሀሳብ ስልጠና እንደሚሰጥ ዶ/ር አባይነህ ገልፀው ሰልጣኞች በቆይታቸው የሚቀስሙትን ግንዛቤና ክህሎት ተግባር ላይ እንዲያውሉ አሳስበዋል።
የወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ ዲን አሉላ ታፈሰ (ዶ/ር) በበኩላቸው ኮሌጁ ከቢሮው ጋር በመተባበር በቀበሌ ደረጃ የሚሠሩ የልማት ጣቢያ ባለሙያዎች ዘንድ የሚስተዋሉ የግንዛቤና ክህሎት ክፍተቶች በጥናት መለየቱን መነሻ በማድረግ ስልጠናው መዘጋጀቱን ተናግረዋል።
ለአራት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው የስልጠና መድረክ ሰልጣኞች በእንስሳት ዝርያ ማሻሻል፣ በዶሮ እርባታ፣ በንብ ማነብ፣ በሥጋ ሀብት፣ በአሳ ሀብት፣ በእንስሳት ጤና አጠባበቅና በሽታ መከላከል፣ በምግብና ሥርዓተ-ምግብ የትኩረት መስኮች ጠቃሚና አስፈላጊ ግንዛቤና ክህሎት ይጨብጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በመድረኩ የወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ ዲን የሆኑትን አሉላ ታፈሰ (ዶ/ር)ን ጨምሮ ተመራማሪዎች፣ መምህራን፣ የክልሉ ግብርና ቢሮ ከፍተኛ ባለሙያዎች እንዲሁም ሰልጣኝ የቀበሌ የእንስሳት እርባታና የእንስሳት ጤና የልማት ጣቢያ ባለሙያዎች መሳተፋቸው ተዘግቧል።
በአያሌው ዘነበ
25/02/2026
20/02/2026
One of the ongoing Government Initiative activities which is the so called "Lemat Tirufat" performance progress in Garda marta district.
08/02/2026
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ እየለማ የሚገኝ የሙዝ ክላስተር በምስል፤
#ከማምረትበላይ
-------------------------
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ስለግብርና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት👇
📌ድረ-ገጽ፦ www.moa.gov.et
***
📌ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/MoAEthiopia
***
📌ዩቲዩብ፦ https://www.youtube.com/
***
📌ቴሌግራም፦ https://t.me/MoAEthiopianews
***
📌ቲዊተር፦ https://x.com/MoA_Ethiopia
***
📌ሊንክድኢን፡- https://shorturl.at/7O6cs
***
📌ቲክቶክ፦ http://www.tiktok.com/
***
📌ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/moa_ethiopia/
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Website
Address
Gamo Zone
Addis Alem
YES