Dilla University

Dilla University

Share

It is an academic institution in Ethiopia.

24/06/2026

ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት ጋር በተያያዘ ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች፣ እስከ ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ቅሬታቸውን ማቅረብ እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

ተፈታኞች በአካል መገኘት ሳያስፈልጋቸው ውጤት ባዩበት https://result.ethernet.edu.et/usernamepage ሊንክ በመግባት “Submit Complaint” የሚለውን አማራጭ በመጫን በኦንላይን ብቻ ማመልከት እንደሚችሉ የተገለጸ ሲሆን፣ የቅሬታ መቀበያ ጊዜው ከሰኔ 17 እስከ ሰኔ 23/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ እንደሚቆይ ተገልጿል።

ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ/ም

23/06/2026

!


Congratulations!

23/06/2026

!


22/06/2026

📍 ቀኑ እየተቃረበ ነው

ውድ ተመራቂዎች፣ ምዕራፍ አንድ የስኬታችሁ በር ሊከፈት ስድስት ቀናቶች ብቻ ቀርተዋል።

እንኳን ደስ አላችሁ!


21/06/2026

Dilla University Graduation Ceremony - 7 Days to Go!

The countdown continues! Only seven days remain until we celebrate the achievements, dreams, and bright futures of our graduates.

📍 The big day is almost here!


Photos from Dilla University's post 20/06/2026

የ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት የጊዜ ሰሌዳ ይፋ ሆነ።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበትን የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አድርጓል። በዚሁ መሠረት በኦንላይን (Computer-based Testing (CBT) የሚፈተኑ ተፈታኞች በስድስት ዙር የሚፈተኑ ሲሆን ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ይፈተናሉ። ከአራተኛ እስከ ስድስተኛ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች የሚፈተኑ ይሆናል።

ፈተናውን በወረቀት የሚፈተኑ ተፈታኞች የተፈጥሮ ሳይንስ በሶስተኛ ዙር ላይ የሚፈተኑ ሲሆን የማህበራዊ ሳይንስ በአራተኛ ዙር በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚፈተኑ ይሆናል። ዝርዝሩን ከሚከተለው ሠንጠረዥ ይመልከቱ።

የፈተና ስርቆትንና ኩረጃን በጋራ እንከላከል!
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

19/06/2026

✨ 8 DAYS TO GO! ✨
=====*****=====

Dilla University proudly invites students, families, alumni, and the community to join us in celebrating the Graduation Ceremony.

With only 8 days left, anticipation fills the air as we prepare to honor the hard work, dedication, and success of our graduates.

Congratulations!

Photos from Dilla University's post 18/06/2026

ከግንባታ ፕሮጀክት ስራ ተቋሯጭ ድርጅቶች እና አማካሪ ድርጅቶች ጋር የሶስትዮሽ ምክክር ተካሄደ
=============************=============

ዲ.ዩ: ሰኔ 10/2018ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)

ከዚህ በፊት የፕሮጀክቶች አፈፃፀምን በተመለከተ በዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት ቀርቦ ውይይት ሲደረግ የሶስትዮሽ መድረክ እንደሚዘጋጅ ፕሬዝዳንቱ በተናገሩት መሠረት፣ በዛሬው ዕለት ከቦርድ ትውውቁ በኃላ የሶስትዮሽ ምክክር ተካሂዷል።

በመድረኩ በግንባታ ላይ የተሰማሩ የኤፍ.ኢ ኮንስትራክሽን እንዲሁም የታዎር ኮንስትራክሽን እና የኤም.ቲ.ቲ አማካሪ ድርጅት የተሳተፉ ሲሆን፣ ግንባታቸው የተጓተቱ ፕሮጀክቶች በፍጥነት ወደ ስራ እንዲመለሱ ፍሬያማ ውይይት ተካሂዷል።

በሀሴዴላ ጊቢ በኤፍ.ኢ ኮንስትራክሽን ተቋራጭ ድርጅት አማካኝነት እየተሰራ የሚገኘው የጊቢ ውስጥ የአስፋልት መንገድ፣ የአጥር እና የዋና መግብያ በር እንዲሁም የቤተ-መጻህፍት ግንባታ ስራ የሚገኝበት ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ በገጠሙት የተለያዩ ተግዳሮቶች ምክንያት የተጓተተ በመሆኑ የነበሩ ክፍተቶችን በማረም ግንባታውን ማስቀጠል በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ የጋራ ምክክር ተደርጓል።

በመድረኩ በሆስፒታል ጊቢ ዘመናዊ የተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ የግንባታ ፕሮጀክት እየገነባ ከሚገኘው የታዎር ኮንስትራክሽን ድርጅት ጋርም ምክክር ተደርጓል።

የግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር በፍቃዱ መኩሪያ በወቅቱ እንደተናገሩት ፕሮጀክቶቹ በፍጥነት ተጠናቀው ወደ ስራ መግባት እንዳለባቸው ጠቁመው፣ የፕሮጀክቶቹን ቀሪ ስራዎች ጥራት ባለው መንገድ በማገባደድ ማስረከብ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ፕሮጀክቶቹ የተጓተቱበት ምክንያት በኮንትራክተሮች አቅም ማነስ፣ በወቅቱ የዋጋ ንረት፣ እንዲሁም የበጀት ውስንነት እና ሌሎችም ምክንያቶች መሆናቸውን የገለፁት ኢንጂነር በፍቃዱ፣ የሪፈራል እና ማስተማሪያ ሆስፒታል ፕሮጀክት ግንባታ እንዲጠናቀቅ የተሰጠው ልዩ ትኩረት ሌሎች ፕሮጀክቶች ለጊዜው ተቀዛቅዘው እንዲቆዩ ማድረጉን ጠቁመዋል።

የሀሴዴላ ጊቢ የዋና መግብያ በር ፕሮጀክትን በተመለከተ በፊት ላይ የነበረው ወደ አስፓልቱ የቀረበና በቂ ቦታ ባለመኖሩ የዲዛይን ማስተካከያ ስራ እንደሚያስፈልግም ኢንጂነር በፍቃዱ ገልፀዋል።

የኤፍ.ኢ ኮንስትራክሽን ተቋራጭ ድርጅት ባለቤትና ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ኤርሚያስ አሰፋ፣ እንዲሁም የታዎር ኮንስትራክሽን ባሌቤትና ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር አቦነህ ገሰሰ አሁን ላይ ተቋሙ እንዲህ አይነት ምክክሮችን እያደረገ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ በማሰቡ አመስግነው፣ በዬትኛውም ሰዓት ላይ ከተቋሙ ጋር በትብብር ለመስራት ለመተባበር ዝግጁ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

የኤም.ቲ.ቲ አማካሪ ድርጅት ሀላፊ የሆኑት ኢንጂነር ተክለጊዮርጊስ አበበ በበኩላቸው፣ የግንባታ መጓተቶች ተቋሙን ብሎም መንግስትን ለአላስፈላጊ ወጪዎች ስለሚዳሪጉ በተቻለ መጠን ክፍያዎችን በየጊዜው በመፈፀም የተጀመሩ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ ክትትል ማድረግ እንደሚያስፈልግ እና መሠል የሶስትዮሽ መድረኮች ቢዘጋጁ መልካም ስለመሆናቸው ጠቁመዋል። ለፕሮጀክቶቹ መጠናቀቅ አስፈላጊውን ሁሉ ቴክኒካል ድጋፎችን እንደሚያደርጉም ተናግረዋል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ቶላሳ ዳዲ (ዶ/ር) የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ኮንትራክተሮች ሰራተኞቻቸውን ወደ ሳይት እንድያስገቡና ስራዎችን እንዲጀምሩ አሳስበዋል።

የሀሴዴላ ጊቢ የዋና መግቢያ በር ዲዛይን ከጊቢው ውበት ጋር መቃኘት እንዳለበት የተናገሩት ዶ/ር ቶላሳ፣ ለቀጣዩ ትውልድ የሚመጥን፣ የፓርኪንግ ቦታን እና ተያያዥ አገልግሎቶችን ያካተተ ለዓይን ማራኪ ስራ እንዲሰራ አጽንዖት ሰጥተዋል።

የሀሴዴላ ጊቢ የውስጥ ለውስጥ የአስፋልት መንገድን ጨምሮ ተጀምረው የቆሙ ፕሮጀክቶች እንዲቀጥሉ ያሳሰቡት ፕሬዝዳንቱ፣ በሆስፒታል ጊቢ እየተገነባ የሚገኘው ዘመናዊ የተማሪዎች የመመገቢያ አዳራሽ ፕሮጀክት በመጠናቀቅ ላይ ስለሚገኝ ቀሪ ስራዎችን በማካተት ፕሮጀክቱ አልቆ ወደስራ እንዲገባ ተናግረዋል።

በመድረኩ የተነሱትን የቤት ስራዎች በመውሰድ ሁሉም ለተግባራዊነቱ እንዲረባረብም ጠይቀዋል። በቀጣይም መሠል የጋራ መድረኮች እንደሚዘጋጁ የፕሮጀክቶች ክትትል እንደሚደረግ ዶ/ር ቶላሳ ገልፀዋል።

=== # # #===


Photos from Dilla University's post 13/06/2026

በኮቾረ ወረዳ የቡና ምርምርና ሰርቶ ማሳያ ማዕከል ላይ ጉብኝት ተደረገ
===========***********===========

ዲዩ: ሰኔ 06/2018ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)

በዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ቶላሳ ዳዲ (ዶ/ር) የተመራ የማኔጅመንት ልዑክ ቡድን በዞኑ በተለያዩ አከባቢዎች ላይ በሚገኙ የዩኒቨርሲቲው የምርምር ማዕከሎች ላይ ጉብኝት እያደረገ ይገኛል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ቶላሳ ዳዲ (ዶ/ር) የመጀመሪያ የመስክ ምልከታቸውን በማድረግ ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ በዩኒቨርሲቲው ስር የሚገኙ የምርምር ማዕከላት ያሉበትን ደረጃ ለማወቅ እንደሆነ ተገልጿል።

የኮቾሬ ወረዳ የብልጽግና ደፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ እና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ዘርሁን አለሙ፣ ልዑኩን እንኳን በሰላም መጥታችሁ በማለት ተቀብለዋቸዋል።

የወረዳው አብዛኛው መሬት በቡና የተሸፈነ መሆኑን ያነሱት ሀላፊው፣ ያለው የቡና ዝርያ ግን የምርታማነት ችግር እንደነበረበት አንስተዋል። ዩኒቨርሲቲው በጥናት የተደገፉ ምርታማነታቸው የተረጋገጡ የቡና ዝርያዎችን ከማከፋፈል ጀምረሮ የተለያዩ ሰርቶ ማሳያ ቦታዎች ላይ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቁመው፣ ለዚህም የዩኒቨርሲቲው አሻራ ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል።

በዞኑ በኮቾሬ ወረዳ ላይ የሚገኘውን የቡና ምርምርና ሰርቶ ማሳያ ማዕከልን የጎበኙ ሲሆን፣ በማዕከሉ ላይ ስላለው አጠቃላይ መረጃን በተመለከተ የቡና ምርምርና ስልጠና ተቋም ዳይሬክተር ዶ/ር አለሙ ደሳ ለልዑኩ ገለፃ አድርገዋል።

ዶ/ር አለሙ በንግግራቸው፣ ዞኑ በከፍተኛ የቡና ምርት የሚታወቅ ቢሆንም ያሉ ዝርያዎች ያረጁ፣ ዝቅተኛ ምርት የሚሰጡ መሆናቸውን ጠቁመው፣ ዩኒቨርሲቲው ይህንን እንደ ክፍተት በመለየት በርካታ የምርምር ስራዎችን ስለመስራቱ አውስተዋል። ዩኒቨርሲቲው የአየር ንብረቱን መቋቋም የሚችሉ ዝርያዎችን በማምጣት ምርታማነትን ለመጨመር ከፍተኛ ስራ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ዩኒቨርሲቲው ከተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ጋር የምርምር ስራዎችን በቅንጅት በመስራት ላይ እንደሚገኝ አንስተው፣ በኮቾረ የሰርቶ ማሳያ የቡና ማሳ ላይም ለተሞክሮ የሚሆኑ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ሀብታሙ ተመስገን (ዶ/ር)፣ በወረዳው በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ጠቁመው፣ በሰርቶ ማሳያ ሳይቱም ላይ ላለፉት ዓመታት የአከባቢውን አርሶአደር ኑሮ ለማሻሻል በቡና ዘርፍ ላይ የተሰራው ስራ አበረታች መሆኑን ጠቁመዋል።

ዩኒቨርሲቲው በቡና ዘርፍ ላይ የልህቀት ማዕከል ለመሆን በተለያዩ ሳይቶች ላይ ከሚሰራቸው የምርምር ስራዎች ጎን ለጎንም በስልጠና ዘርፉ ላለፉት በርካታ ዓመታት በርካታ ሰልጣኞችን በቡና ስልጠና ማብቃቱን የጠቆሙት ዶ/ር ሀብታሙ፣ ይህም ዩኒቨርሲቲው በዘርፉ ላይ መሪ ተዋናይ ለመሆን እያደረገ ላለው ስራ አንዱ ማሳያ መሆኑን ጠቁመዋል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ቶሎሳ ዳዲ በጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩት፣ እንዲህ ዓይነት ተግባራት ከዩኒቨርሲቲዎች የሚጠበቅ ስራ መሆኑን ጠቁመው፣ ቡና ትልቁ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንትና አረንጓዴ ወርቅ ከሚባሉ ሀብቶች መካከል አንዱ በመሆኑ በዘርፉ ላይ የተቻለንን ሁሉ ማድረግ ይገባል ብለዋል። ቡና የውጭ ምንዛሬን በማምጣት ረገድም ከፍተኛ ሚና ያለው ሀብት በመሆኑ የበለጠ ልንመራመር ይገባል ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ።

የቡና ምርታማነት እንድያድግ እና የሀገርን ኢኮኖሚ እንድያግዝ የተሰራው ስራ እጅግ የሚያኮራ መሆኑን እና ዩኒቨርሲቲው በሳይቱ ላይ የሰራውን ስራ ያደነቁት ፕሬዝዳንቱ፣ ከሁሉ በላይ ደግሞ የአከባቢው ማህበረሰብ እና የዩኒቨርሲቲው ቅንጅት ለዚህ ስራ ትልቅ አስተዋጽዖ ማድረጉን አንስተዋል።

የቡና ምርት ሰባት እና ከዚያ ዓመት በላይ ሳይጠበቅ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለፍሬ እንዲበቃ የተሰራው ፕሮጀክት የሚያኮራ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፣ በዚህ ስራ ውስጥ አስተዋጽዖ የነበራቸው ሁሉም አካላትን አመስግነዋል። ስራውን የበለጠ ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

በጉብኝቱ ላይ የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት አባላት እና ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የወረዳው የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

=== # # #===


Want your school to be the top-listed School/college in Dilla?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Dilla