Dilla University

Dilla University

Share

Dilla University, often referred as 'University of the Greenland' due to the greenery in and around.

Photos from Dilla University's post 18/06/2026

Dilla University Hosts PhD Dissertation Defense
===========************===========

DU, June 18, 2026 (PIR)

Four PhD candidates from Dilla University’s Institute of Education and Behavioral Studies successfully defended their dissertations in a session that drew academics, researchers, educators, and guests.

In his Opening remark, Dr. Tamrat Beyene, Vice President for Academic Affairs, hailed the defense as a milestone for the college, underscoring ongoing efforts to meet societal needs, expand access to education, and improve quality.

He stressed that producing competent professionals is key to solving national challenges. Dr. Tamrat also commended the candidates for their dedication and contributions to Ethiopia’s educational research and policy development.

Dean, Institute of Education and Behavioral Studies Dr. Birhanu Mekonnen welcomed participants and highlighted the importance of doctoral research in advancing knowledge and strengthening the university’s academic excellence.

The session featured presentations from:

📍 Mesay Mahabera — PhD in Curriculum and Teacher Education

📍 Zerihun Ayalew Gebre — PhD in Educational Psychology

📍Zinabu Tesfaye Gajabo — PhD in Educational Policy and Leadership

📍Adan Hussein Mohamed — PhD in Educational Policy and Leadership

Dilla University congratulated the candidates, wishing them success as they continue contributing to scholarship and national development.

=== # # #===

Photos from Dilla University's post 18/06/2026

📍ማስታወቂያ 📍
====***====

በነገው ዕለት ማለትም በቀን 12/10/2018ዓ.ም በሶስቱም መርሃ ግብሮች የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ዝርዝር መረጃዎችን በተመለከተ ከስር በተቀመጠው ሰንጠረዥ ላይ ማየት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።


18/06/2026

📍 እንኳን ደስ አላችሁ 📍
====*******====

ዲላ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ሰኔ 20/2018ዓ.ም በደማቅ ስነ-ስርዓት ያስመርቃል።

ውድ ተመራቂዎች፣ እነሆ የልፋታችሁን ፍሬ የምታዩበት ያቺ ቀን ተቃርባለችና እንኳን ደስ አላችሁ።

📍 ወላጆች እና ጓደኞች - ማንን "እንኳን ደስ አለሽ/አለክ" ማለት ይፈልጋሉ?

📍 ተመራቂዎች - ለናንተ እዚህ ደረጃ መድረስ ማንን ያመሰግናሉ?

እንኳን ደስ አላችሁ፣ የመጀመሪያው የህይወታችሁ የስኬት ምዕራፍ እነሆ ጀምሯል።

🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅

Dilla University will proudly host its Graduation Ceremony On June 27, 2026.

Dear Graduates, the day you have long awaited - the day to reap the fruits of your hard work is finally approaching. Congratulations!

📍 Parents and Friends: Whom do you wish to say “Congratulations” to on this special day?

📍 Graduates: Whom do you wish to thank for guiding you to this milestone?

Congratulations! This marks the beginning of the very first chapter of your life’s success story.

=== # # #===


Photos from Dilla University's post 17/06/2026

ከግንባታ ፕሮጀክት ስራ ተቋሯጭ ድርጅቶች እና አማካሪ ድርጅቶች ጋር የሶስትዮሽ ምክክር ተካሄደ
=============************=============

ዲ.ዩ: ሰኔ 10/2018ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)

ከዚህ በፊት የፕሮጀክቶች አፈፃፀምን በተመለከተ በዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት ቀርቦ ውይይት ሲደረግ የሶስትዮሽ መድረክ እንደሚዘጋጅ ፕሬዝዳንቱ በተናገሩት መሠረት፣ በዛሬው ዕለት ከቦርድ ትውውቁ በኃላ የሶስትዮሽ ምክክር ተካሂዷል።

በመድረኩ በግንባታ ላይ የተሰማሩ የኤፍ.ኢ ኮንስትራክሽን እንዲሁም የታዎር ኮንስትራክሽን እና የኤም.ቲ.ቲ አማካሪ ድርጅት የተሳተፉ ሲሆን፣ ግንባታቸው የተጓተቱ ፕሮጀክቶች በፍጥነት ወደ ስራ እንዲመለሱ ፍሬያማ ውይይት ተካሂዷል።

በሀሴዴላ ጊቢ በኤፍ.ኢ ኮንስትራክሽን ተቋራጭ ድርጅት አማካኝነት እየተሰራ የሚገኘው የጊቢ ውስጥ የአስፋልት መንገድ፣ የአጥር እና የዋና መግብያ በር እንዲሁም የቤተ-መጻህፍት ግንባታ ስራ የሚገኝበት ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ በገጠሙት የተለያዩ ተግዳሮቶች ምክንያት የተጓተተ በመሆኑ የነበሩ ክፍተቶችን በማረም ግንባታውን ማስቀጠል በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ የጋራ ምክክር ተደርጓል።

በመድረኩ በሆስፒታል ጊቢ ዘመናዊ የተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ የግንባታ ፕሮጀክት እየገነባ ከሚገኘው የታዎር ኮንስትራክሽን ድርጅት ጋርም ምክክር ተደርጓል።

የግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር በፍቃዱ መኩሪያ በወቅቱ እንደተናገሩት ፕሮጀክቶቹ በፍጥነት ተጠናቀው ወደ ስራ መግባት እንዳለባቸው ጠቁመው፣ የፕሮጀክቶቹን ቀሪ ስራዎች ጥራት ባለው መንገድ በማገባደድ ማስረከብ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ፕሮጀክቶቹ የተጓተቱበት ምክንያት በኮንትራክተሮች አቅም ማነስ፣ በወቅቱ የዋጋ ንረት፣ እንዲሁም የበጀት ውስንነት እና ሌሎችም ምክንያቶች መሆናቸውን የገለፁት ኢንጂነር በፍቃዱ፣ የሪፈራል እና ማስተማሪያ ሆስፒታል ፕሮጀክት ግንባታ እንዲጠናቀቅ የተሰጠው ልዩ ትኩረት ሌሎች ፕሮጀክቶች ለጊዜው ተቀዛቅዘው እንዲቆዩ ማድረጉን ጠቁመዋል።

የሀሴዴላ ጊቢ የዋና መግብያ በር ፕሮጀክትን በተመለከተ በፊት ላይ የነበረው ወደ አስፓልቱ የቀረበና በቂ ቦታ ባለመኖሩ የዲዛይን ማስተካከያ ስራ እንደሚያስፈልግም ኢንጂነር በፍቃዱ ገልፀዋል።

የኤፍ.ኢ ኮንስትራክሽን ተቋራጭ ድርጅት ባለቤትና ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ኤርሚያስ አሰፋ፣ እንዲሁም የታዎር ኮንስትራክሽን ባሌቤትና ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር አቦነህ ገሰሰ አሁን ላይ ተቋሙ እንዲህ አይነት ምክክሮችን እያደረገ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ በማሰቡ አመስግነው፣ በዬትኛውም ሰዓት ላይ ከተቋሙ ጋር በትብብር ለመስራት ለመተባበር ዝግጁ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

የኤም.ቲ.ቲ አማካሪ ድርጅት ሀላፊ የሆኑት ኢንጂነር ተክለጊዮርጊስ አበበ በበኩላቸው፣ የግንባታ መጓተቶች ተቋሙን ብሎም መንግስትን ለአላስፈላጊ ወጪዎች ስለሚዳሪጉ በተቻለ መጠን ክፍያዎችን በየጊዜው በመፈፀም የተጀመሩ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ ክትትል ማድረግ እንደሚያስፈልግ እና መሠል የሶስትዮሽ መድረኮች ቢዘጋጁ መልካም ስለመሆናቸው ጠቁመዋል። ለፕሮጀክቶቹ መጠናቀቅ አስፈላጊውን ሁሉ ቴክኒካል ድጋፎችን እንደሚያደርጉም ተናግረዋል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ቶላሳ ዳዲ (ዶ/ር) የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ኮንትራክተሮች ሰራተኞቻቸውን ወደ ሳይት እንድያስገቡና ስራዎችን እንዲጀምሩ አሳስበዋል።

የሀሴዴላ ጊቢ የዋና መግቢያ በር ዲዛይን ከጊቢው ውበት ጋር መቃኘት እንዳለበት የተናገሩት ዶ/ር ቶላሳ፣ ለቀጣዩ ትውልድ የሚመጥን፣ የፓርኪንግ ቦታን እና ተያያዥ አገልግሎቶችን ያካተተ ለዓይን ማራኪ ስራ እንዲሰራ አጽንዖት ሰጥተዋል።

የሀሴዴላ ጊቢ የውስጥ ለውስጥ የአስፋልት መንገድን ጨምሮ ተጀምረው የቆሙ ፕሮጀክቶች እንዲቀጥሉ ያሳሰቡት ፕሬዝዳንቱ፣ በሆስፒታል ጊቢ እየተገነባ የሚገኘው ዘመናዊ የተማሪዎች የመመገቢያ አዳራሽ ፕሮጀክት በመጠናቀቅ ላይ ስለሚገኝ ቀሪ ስራዎችን በማካተት ፕሮጀክቱ አልቆ ወደስራ እንዲገባ ተናግረዋል።

በመድረኩ የተነሱትን የቤት ስራዎች በመውሰድ ሁሉም ለተግባራዊነቱ እንዲረባረብም ጠይቀዋል። በቀጣይም መሠል የጋራ መድረኮች እንደሚዘጋጁ የፕሮጀክቶች ክትትል እንደሚደረግ ዶ/ር ቶላሳ ገልፀዋል።

=== # # #===


Photos from Dilla University's post 17/06/2026

📍ማስታወቂያ 📍
===******===

በቀን 11/10/2018ዓ.ም በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፈተና ማዕከል በመጀመሪያው፣ ሁለተኛው እና ሶስተኛው ዙር ( , and ) ላይ የመውጫ ፈተና የምትወስዱ ተፈታኞች፣ የመፈተኛ ቦታ እና ተያያዥ መረጃዎችን ከስር ከተቀመጠው ሰንጠረዥ ላይ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

ለፈተና ሲመጡ የፋይዳ መታወቂያ፣ የዩኒቨርሲቲ መታወቂያ እንዲሁም የፈተና መግብያ ቲኬት ይዘው መገኘት ይጠበቅባችኋል።

ለተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ መልካም እድል እንዲገጥማችሁ እንመኛለን።

መረጃውን ለተፈታኝ ጓደኞችዎ ያጋሩ! የፈተናን ህግና ደንብ ያክብሩ!


Photos from Dilla University's post 17/06/2026

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ቶላሳ ዳዲ (ዶ/ር) ከዩኒቨርሲቲው የስራ አመራር ቦርድ ጋር ትውውቅ አደረጉ
============***********=============

ዲ.ዩ: ሰኔ 10/2018ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ቶላሳ ዳዲ (ዶ/ር) ከዩኒቨርሲቲው የስራ አመራር ቦርድ ጋር የትውውቅ መርሃ ግብር አድርገዋል።

በትውውቅ መድረኩ ላይ የዩኒቨርሲቲው የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ለአዲሱ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸው በመመኘት፣ ዩኒቨርሲቲው የያዛቸውን ግቦች እንዲያሳካ የስራ አመራር ቦርዱ ከአዲሱ አመራር ጋር በቅርበት እንደሚሰራ ቃል ገብተዋል።

አዲሱ ፕሬዝዳንትም የተጀመሩ መልካም ስራዎችን እንድያስቀጥሉ፣ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ በትጋት እንዲሰሩ ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ቶላሳ ዳዲ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ የስራ አመራር ቦርዱ የትውውቅ መድረኩን በማዘጋጀቱ አመስግነው፣ የተሻለ ተቋማዊ አፈፃፀም እንዲኖር ከቦርዱ እንዲሁም ከመላው የዩኒቨርሲቲው አመራር እና ማህበረሰብ ጋር ተቀናጅተው ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በመድረኩ ላይ የዩኒቨርሲቲው የስራ አመራር ቦርድ አባላት ተገኝተዋል።

=== # # #===


Photos from Dilla University's post 16/06/2026

ለህግ ባለሙያዎች እና ለፍትህ ባለድርሻ አካላት ስልጠና ተሰጠ
=============*************============

ዲ.ዩ: ሰኔ 09/2018ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)

የዲለ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት በተጎጂዎች የስነ-ልቦና ጉዳት እና በፍትህ ስርዓት ዙሪያ ላይ ለህግ ባለሙያዎች እና ለፍትህ ባለድርሻ አካላት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሰጥቷል።

ስልጠናው የተሰጠው ከአውሮፖ ህብረት እና ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአደገኛ መድሃኒቶች እና ወንጀል መከላከል ድርጅት (UNODC) ጋር በመተባበር ነዉ።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት ዲን እና የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ሀይለማርያም ማሞ እንደተናገሩት፣ በፍትህ ስርዓቱ ውስጥ የሚያጋጥሙ የስነ ልቦና ጉዳቶችን ለመቀነስ ብሎም በሂደቱ ተጋላጭ እና ተጎጂ የሚሆኑ ወገኖችን መጠበቅ በሚቻልበት መንገዶች ላይ የተዘጋጀ ስልጠና እንደሆነ ተናግረዋል።

አክለውም የፍትህ ስርዓቱ በግለሰቦች ስነልቦና ላይ ጠባሳ ጥሎ የሚያልፍ ወንጀል ሲፈፀም ፖሊስ፣ ዐቃቤ ህግ፣ ፍርድ ቤት እና ሌሎችም አካላት የስነልቦና ጉዳቱን በማያባብስ መልኩ እንዴት ማስተናገድ እንዳለባቸው ግንዛቤ የሚሰጥ እንደሆነም ተናግረዋል።

የዲላ ዩኒቨርስቲ ነፃ የህግ ድጋፍ ማዕከላት አስተባባሪ እና የፕሮጀክት ስልጠናዎች ኦፊሰር መምህርት የምስራች ያለው በበኩላቸው፣ ተገልጋዮች የህግ አገልግሎት ለማግኘት ከሚያመጣቸው ምክንያት ጋር በተያያዘ የሚመጣባቸዉ የስነልቦና ጉዳት እና ጫናን ለመቀነስ፣ አገልግሎት ሰጪዎች እንዲሁም በፍትህ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ አካላት የተገልጋዮች አያያዝ ላይ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማስቻል ታስቦ ስልጠናው መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

ስልጠናዉን ከሰጡት ባለሙያዎች መካከል በዲለ ዩኒቨርስቲ የህግ ትምህርት ቤት መምህርት ስንታየሁ ፍቅሩ እንደገለፁት፣ የስነልቦና ጉዳትን ያማከለ የህግ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሠረታዊ ፅንስ ሃሳብ እና መርሆዎችን እንዲሁም የኢትዮጵያ የህግ ማዕቀፍን በተመለከተ ስልጠና መስጠታቸውን ገልጸዋል።

ስልጠናዉን የወሰዱ ሰልጣኞችም ትክክለኛ ፍትህን ተደራሽ ለማድረግ ብሎም በሂደቱ የዜጎች ስነ ልቦና እንዲጠበቅ እና የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ የጥንቃቄ መንገዶችን ለመውሰድ የሚረዱ እውቀቶችን ስለማግኘታቸው አውስተዋል።

በስልጠናው ከ50 በላይ የሚሆኑ በደቡብ ኢትዮጵያ በጌድኦ ዞን፣ ሲዳማና ኦሮሚያ ክልል ወረዳዎች የሚገኙ ዳኞች፣ አቃቤ ህጎች፣ ነፃ የህግ ድጋፍ የሚሰጡ ባለሙያዎች፣ የፖሊስ አካላት፣ የማረሚያ ቤት ሀላፊዎች እንዲሁም የሴቶችና ህፃናት ጽህፈት ቤት ሀላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

=== # # #===


Photos from Dilla University's post 16/06/2026

📍ማስታወቂያ 📍

በነገው ዕለት ማለትም በቀን 10/10/2018ዓ.ም በሚሰጠው የመውጫ ፈተና በሁለተኛው እና ሶስተኛው መርሃግብር ( and ) ላይ የምትፈተኑ ተፈታኞች፣ የመፈተኛ ቦታ እና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎችን ከስር ባለው ሰንጠረዥ ላይ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

መልካም ፈተና


Photos from Dilla University's post 16/06/2026

📍ማስታወቂያ 📍
===******===

በቀን 10/10/2018ዓ.ም በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፈተና ማዕከል በመጀመሪያው ዙር ( ) ላይ የመውጫ ፈተና የምትወስዱ ተፈታኞች፣ የመፈተኛ ቦታ እና ተያያዥ መረጃዎችን ከስር ከተቀመጠው ሰንጠረዥ ላይ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

ለፈተና ሲመጡ የፋይዳ መታወቂያ፣ የዩኒቨርሲቲ መታወቂያ እንዲሁም የፈተና መግብያ ቲኬት ይዘው መገኘት ይጠበቅባችኋል።

ለተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ መልካም እድል እንዲገጥማችሁ እንመኛለን።

መረጃውን ለተፈታኝ ጓደኞችዎ ያጋሩ! የፈተናን ህግና ደንብ ያክብሩ


Photos from Dilla University's post 15/06/2026

📍ማስታወቂያ 📍
===******===

ለተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ

በቀን ዐ9/10/2018ዓ.ም በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፈተና ማዕከል በሁለተኛውና ሶስተኛው ዙር ( and ) ላይ የመውጫ ፈተና የምትወስዱ ተፈታኞች፣ የመፈተኛ ቦታ እና ተያያዥ መረጃዎችን ከስር ከተቀመጠው ሰንጠረዥ ላይ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

ለፈተና ሲመጡ የፋይዳ መታወቂያ፣ የዩኒቨርሲቲ መታወቂያ እንዲሁም የፈተና መግብያ ቲኬት ይዘው መገኘት ይጠበቅባችኋል።

ለተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ መልካም እድል እንዲገጥማችሁ እንመኛለን።

መረጃውን ለተፈታኝ ጓደኞችዎ ያጋሩ! የፈተናን ህግና ደንብ ያክብሩ


Want your school to be the top-listed School/college in Dilla?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address


South Ethiopia Region
Dilla
419

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:30
Tuesday 08:00 - 17:30
Wednesday 08:00 - 17:30
Thursday 08:00 - 17:30
Friday 08:00 - 17:30
Saturday 08:00 - 17:30